Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ኢዩ የሰማርያን ሕዝብ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ንጉሥ አክዓብ በዓልን ያገለገለው በመጠኑ ነበር፤ እኔ ግን ከእርሱ ይበልጥ ላገለግለው እፈልጋለሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም ኢዩ ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት ሰብስቦ እንዲህ አለ፤ “አክዓብ በኣልን ያገለገለው በጥቂቱ ነው፤ ኢዩ ግን ይበልጥ ያገለግለዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ኢዩ የሰማርያን ሕዝብ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ንጉሥ አክዓብ ባዓልን ያገለገለው በመጠኑ ነበር፤ እኔ ግን ከእርሱ ይበልጥ ላገለግለው እፈልጋለሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ኢዩም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ፥ “አክ​አብ በዓ​ልን በጥ​ቂቱ አመ​ለ​ከው፤ ኢዩ ግን በብዙ ያመ​ል​ከ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ኢዩም ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ “አክዓብ በኣልን በጥቂቱ አመለከው፤ ኢዩ ግን በብዙ ያመልከዋል።

参见章节 复制




2 ነገሥት 10:18
9 交叉引用  

ይልቅስ አሁን እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፤ በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያትንና አራት መቶ የአሼራ ነቢያትን ጭምር ይዘህ ና።”


ከዚህ በኋላ ኤልያስ እንዲህ አለ፦ “ከጌታ ነቢያት የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያት ግን እነሆ በዚህ አሉ፤


ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ፤ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።


የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ በመጣስ የሚሰግዱላቸውን ከወርቅ የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፤ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፤ ለከዋክብት ሰገዱ፤ በዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ።


እርሱም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ ይሁን እንጂ እርሱ የአባቱንና የእናቱን የኤልዛቤልን ያኽል መጥፎ ሰው አልነበረም፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውን ባዕድ አምላክ ለማምለክ አባቱ አሠርቶት የነበረውን ምስል አስወገደ፤


በውኑ ስለ እግዚአብሔር ሐሰትን ትናገራላችሁን? ስለ እርሱም ሽንገላን ታወራላችሁን?


“መልካም ነገር እንዲመጣ ለምን ክፉ አናደርግም?” ይላሉ ብለው እንደሚያሙን አይደለም፤ የሚፈረድባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው።


በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ክቡር የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ምስጉን የሆነውን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤


跟着我们:

广告


广告