Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 36:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የጌታንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የሹማምንቱን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እርሱም ትልልቁንም ሆነ ትንንሹን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃ በሙሉ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሀብት፣ የንጉሡንና የሹማምቱን ሀብት ሁሉ ወደ ባቢሎን አጋዘ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የቤተ መቅደሱን፥ የንጉሡንና የእርሱ ባለሟሎች የሆኑትን ባለሥልጣኖች ግምጃ ቤት በሙሉ ዘርፎ ወደ ባቢሎን ወሰደ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የአ​ለ​ቆ​ቹ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ወሰደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የአለቆቹን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 36:18
10 交叉引用  

ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።


ናቡከደናፆርም ከጌታ ቤት ዕቃ አያሌውን ወደ ባቢሎን አጋዘ፥ በባቢሎንም በመቅደሱ ውስጥ አኖረው።


እነሆ፥ በቤትህ ያለውን ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል ጌታ።


ዮድ። አስጨናቂው በከበረ ነገርዋ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፥ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።


ነገር ግን ለአገልጋዮቼ ለነቢያት ያዘዝኳቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? ከዚያ እነርሱም ተጸጽተው፦ “የሠራዊት ጌታ በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ሊያደርግብን ያሰበውን እንዲሁ አድርጎብናል” በማለት ተቀበሉ።


跟着我们:

广告


广告