Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 35:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኒካዑም እንዲህ ብሎ መልእክተኞችን ላከበት፦ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ውግያ የማደርገው በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ አልመጣሁም፤ ጌታም እንድቸኩል አዝዞኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው ጌታ እንዳያጠፋህ ይህን በእርሱ ላይ ከማድረግ ተመለስ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ኒካዑ ግን መልእክተኛውን ልኮ፣ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፤ አንተንና እኔን የሚያጣላን ምንድን ነው? ጦርነት ከገጠምሁት ቤት ጋራ እንጂ በአሁኑ ጊዜ አንተን የምወጋህ አይደለሁም፤ እግዚአብሔር እንድፈጥን አዝዞኛል፤ ስለዚህ ከእኔ ጋራ ያለውን እግዚአብሔርን መቃወምህን ተው፤ አለዚያ ያጠፋሃል” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኒካዑ ግን ለኢዮስያስ “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ እኔንና አንተን የሚያጣላን ምንም ነገር የለም፤ እኔ የመጣሁት ጠላቶቼን ለመውጋት እንጂ፥ አንተን ለመውጋት አይደለም፤ ጠላቶቼንም በፍጥነት እንድወጋ እግዚአብሔር አዞኛል፤ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ስለ ሆነ፥ ባትቃወመኝ ይሻልሃል፤ እምቢ ብትል ግን እግዚአብሔር ያጠፋሃል” የሚል መልእክት ላከበት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እር​ሱም፥ “የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? በም​ዋ​ጋ​በት በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአ​ንተ ላይ ዛሬ አል​መ​ጣ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ድ​ቸ​ኩል አዝ​ዞ​ኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋህ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ​በት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እርሱም “የይሁዳ ንጉሥ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? በምዋጋበት በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ አልመጣሁም፤ እግዚአብሔርም እንድቸኵል አዝዞኛል፤ ከእኔ ጋር ያለው እግዚአብሔር እንዳያጠፋህ ይህን በእርሱ ላይ ከማድረግ ተመለስ” ብሎ መልእክተኞችን ላከበት።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 35:21
7 交叉引用  

ንጉሡ ግን፥ “እናንት የጽሩያ ልጆች እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ጌታ፥ ‘ዳዊትን ርገመው’ ብሎት የሚረግመኝ ከሆነ፥ ‘ይህን ለምን አደረግህ’ ብሎ ማን ሊጠይቀው ይችላል?” አለው።


እኔ በአንተ አገር ላይ አደጋ የጣልኩባትና የደመሰስኳት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እግዚአብሔር ራሱ በዚህች አገር ላይ አደጋ እንድጥልባትና እንድደመስሳት አዞኛል።”


አንተም፦ ‘እነሆ፥ ኤዶምያስን መትቻለሁ’ ብለህ ኰርተሃል፤ በቤትህ ተቀመጥ፤ አንተ ከይሁዳ ጋር አብረህ ለመውደቅ ለምን መከራ ትሻላህ?”


ኢዮስያስ ግን ማንነቱን ሸሽጎ ለመዋጋት ወጣ እንጂ ፊቱን ከእርሱ አልመለሰም፤ በጌታም አፍ የተነገረውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፥ በመጊዶም ሸለቆ ለመዋጋት መጣ።


አሁንም ቢሆን፥ ጌታ፦ ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው አለኝ እንጂ፥ በውኑ ያለ ጌታ ይህን አገር ለማጥፋት የዘመትኩ ይመስልሃል?”


እነሆ እንዲህ እያሉ ጮኹ “የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?”


ኢየሱስም “አንቺ ሴት ሆይ፦ ይህ ጉዳይ ለእኔ ምንድነው? ጊዜዬ ገና አልደረሰም፤” አላት።


跟着我们:

广告


广告