2 ዜና መዋዕል 29:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ንጉሡም ሕዝቅያስና ሹማምንቱ ሌዋውያንን በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል ጌታን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። በደስታም እያመሰገኑ፥ አጐነበሱም ሰገዱም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ንጉሥ ሕዝቅያስና ሹማምቱ፣ ሌዋውያኑ በዳዊትና በባለራእዩ በአሳፍ ቃል እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። እነርሱም ውዳሴውን በደስታ ዘመሩ፤ ራሳቸውንም አጐንብሰው ሰገዱ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 ንጉሡና የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ በዳዊትና በነቢዩ አሳፍ የተደረሱትን የምስጋና መዝሙሮች ለእግዚአብሔር ክብር እንዲዘምሩ ሌዋውያንን አዘዙ፤ ስለዚህ ሁሉም ተንበርክከው በመስገድ ላይ ሳሉ በታላቅ ደስታ ይዘምሩ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ንጉሡ ሕዝቅያስና አለቆቹም በዳዊትና በነቢዩ በአሳፍ ቃል እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ሌዋውያንን አዘዙ። በደስታም አመሰገኑ፤ አጐነበሱም፤ ሰገዱም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ንጉሡም ሕዝቅያስና አለቆቹ ሌዋውያንን በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ አዘዙ። በደስታም አመሰገኑ፤ አጎነበሱ፤ ሰገዱም። 参见章节 |