Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 29:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ካህናቱም መቅደሱን ለማንጻት ወደ ጌታ ቤት ወደ ውስጡ ገቡ፥ በጌታም መቅደስ ያገኙትን ርኩስ ነገር ሁሉ ወደ ጌታ ቤት አደባባይ አወጡት። ሌዋውያንም ወስደው ወደ ሜዳ ወደ ቄድሮን ወንዝ ጣሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ካህናቱ የእግዚአብሔርን መቅደስ ለማንጻት ወደ ውስጡ ገቡ። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ያገኙትንም ማንኛውንም የረከሰ ነገር ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ አወጡት። ሌዋውያኑም ተሸክመው በመውሰድ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ ጣሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ካህናቱም ቤተ መቅደሱን ለማንጻት ወደ ውስጡ ገቡ፤ ያልነጻውንም ነገር ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ አወጡት፤ ሌዋውያኑም ከዚያ አንሥተው ከከተማ ውጪ በመውሰድ በቄድሮን ሸለቆ ጣሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ካህ​ና​ቱም ያነ​ጹት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስጥ ገቡ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መቅ​ደስ ያገ​ኙ​ትን ርኩስ ነገር ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ አወ​ጡት። ሌዋ​ው​ያ​ንም ወስ​ደው ወደ ሜዳ ወደ ቄድ​ሮን ወንዝ ጣሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ካህናቱም ያነጹት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጡ ገቡ፤ በእግዚአብሔርም መቅደስ ያገኙትን ርኩስ ነገር ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት አደባባይ አወጡት። ሌዋውያንም ወስደው ወደ ሜዳ ወደ ቄድሮን ወንዝ ጣሉት።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 29:16
15 交叉引用  

ሕዝቡ ሁሉ በሚያልፍበትም ጊዜ ባላገሩ በሙሉ እየጮኸ አለቀሰ፤ ንጉሡም የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ተሻግሮ ወደ ምድረ በዳው አመሩ።


ንጉሡም አሳ እናቱን መዓካን በማምለኪያ ዐፀድ ጣዖት ስላደረገች ከእቴጌነትዋ ሻራት፤ አሳም ምስልዋን ቈርጦ ቀጠቀጠው፥ በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው።


ቅድስተ ቅዱሳኑንም ሠራ፤ ርዝመቱም እንደ ቤቱ ወርድ ሀያ ክንድ፥ ወርዱም ሀያ ክንድ ነበረ፤ ስድስት መቶ መክሊት በሚያህል በጥሩ ወርቅ ለበጠው።


ተነሥተውም በኢየሩሳሌም የነበሩትን መሠዊያዎችና ለጣዖታት የሚያጥኑበትን ዕቃ ሁሉ አስወገዱ፥ በቄድሮንም ወንዝ ጣሉት።


ካህናቱም የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቱ አምጥተው በመቅደሱ በውስጠኛው ክፍል በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ከኪሩቤል ክንፍ በታች በነበረው በስፍራው አኖሩት።


ጓዳዎቹንም እንዲያነጹ አዘዝሁ፥ የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃዎች የእህሉንም ቁርባን ዕጣኑንም መልሼ በዚያ አገባሁ።


ከርኩሰታችሁ ሁሉ አድናችኋለሁ፤ እህሉን እጠራዋለሁ አበዛዋለሁም፥ ረኃብም አላመጣባችሁም።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን!ወዮላችሁ፥ በውጫቸው አምረው የሚታዩ በውስጣቸው ግን በሙታን አጥንትና በርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ትመስላላችሁና።


ኢየሱስም ይህን ብሎ አትክልት ወዳለበት ስፍራ ወደ ቄድሮን ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ እርሱም ደቀ መዛሙርቱም በዚያ ገቡ።


跟着我们:

广告


广告