Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 28:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አካዝም ከጌታ ቤት ከንጉሡና ከአለቆቹም ቤት እኩሌታውን ገፈፈ፥ ለአሦርም ንጉሥ ሰጠ፤ ነገር ግን እንዲህ ማድረጉ አንዳች አልጠቀመውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አካዝም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ከቤተ መንግሥቱና ከመሳፍንቱ ዕቃዎች ዘርፎ ለአሦር ንጉሥ ሰጥቶት ነበር፤ ነገር ግን አልረዳውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ስለዚህ አካዝ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፥ ከቤተ መንግሥቱና ከሕዝቡ መሪዎች ዘንድ ብዙ ወርቅ ወስዶ ለንጉሠ ነገሥቱ መማለጃ አድርጎ ሰጠ፤ ይሁን እንጂ ይህን ማድረጉም አልጠቀመውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አካ​ዝም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከን​ጉ​ሡና ከአ​ለ​ቆ​ቹም ቤት የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ለአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰጠ፥ ነገር ግን አስ​ጨ​ነ​ቀው እንጂ አል​ረ​ዳ​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አካዝም ከእግዚአብሔር ቤት ከንጉሡና ከአለቆቹም ቤት እኵሌታውን ገፈፈ፤ ለአሦርም ንጉሥ ሰጠ፤ ነገር ግን አንዳች አልተጠቀመበትም።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 28:21
8 交叉引用  

የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ የጌታንም ቤት መዛግብትና የንጉሡን ቤት መዛግብት ወሰደ፤ ሁሉንም ነገር ወሰደ፤ ደግሞም ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻዎች ወሰደ።


አሳም ከጌታ ቤትና ከንጉሡ ቤት መዝገብ ብርና ወርቅ ወስዶ በደማስቆ ወደ ተቀመጠው ወደ ሶሪያ ንጉሥ ወደ ወልደ አዴር እንዲህ ብሎ ላከ፦


ሰው በችኰላ፦ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ነው።


ከሃዲን ሰው በመከራ ጊዜ መተማመን እንደ ተሰበረ ጥርስና እንደ ሰለለ እግር ነው።


መንገድሽን ለመለወጥ ለምን በጣም ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ እንዲሁ ያሳፍርሻል።


ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።


跟着我们:

广告


广告