Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 25:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የይሁዳም ንጉሥ አሜስያስ ተማክሮ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ኢዮአስ እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ና፥ እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ አማካሪዎቹን ካማከረ በኋላ፣ የእስራኤል ንጉሥ የኢዩ የልጅ ልጅ፣ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ ኢዮአስ፣ “ናና ፊት ለፊት እንጋጠም” ሲል ላከበት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከዚህ በኋላ ንጉሥ አሜስያስና አማካሪዎቹ በእስራኤል ላይ አሤሩ፤ አሜስያስም የኢዩ የልጅ ልጅ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ እስራኤል ንጉሥ ዮአስ መልእክተኞች በመላክ “እንግዲህ፥ ና ይዋጣልን?” ሲል ለጦርነት አነሣሣው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አሜ​ስ​ያስ ምክር አደ​ረ​ገና፥ “ና፥ እርስ በር​ሳ​ችን ፊት ለፊት እን​ተ​ያይ” ብሎ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮ​አ​ካዝ ልጅ ወደ ኢዮ​አስ ላከ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የይሁዳም ንጉሥ አሜስያስ ምክር አደረገና “ና፥ እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ኢዮአስ ላከ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 25:17
7 交叉引用  

ከዚያም አበኔር፥ ኢዮአብን፥ “ጉልማሶች ይነሡና በፊታችን ትግል ይግጠሙ” አለው። ኢዮአብም፥ “ይሁን እሺ ይግጠሙ” ብሎ መለሰ።


አሜስያስ ግን ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄዱ ያሰናበታቸው ጭፍሮች ከሰማርያ ጀምረው እስከ ቤትሖሮን ድረስ በይሁዳ ከተሞች ላይ አደጋ ጣሉ፥ ከእነርሱም ሦስት ሺህ ሰዎች ገደሉ፥ ብዙ ምርኮም ማረኩ።


እርሱም እየተናረ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በውኑ አንተ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሾመነሃልን? ተው፤ እንዲገድሉህ ለምን ትሻለህ?” ነቢዩም፦ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና ጌታ ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ተወ።


ከክርክር ይርቅ ዘንድ ለሰው ክብሩ ነው፥ ሰነፍ ሁሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል።


ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፤ ዮሴፍና እናቱም አላወቁም ነበር።


ዳዊት በልቡ፦ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፥ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ አሰበ።


跟着我们:

广告


广告