Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 22:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከሶርያም ንጉሥ ከአዛኤል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቁስል ለመታከም ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፤ ታምሞም ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ለማየት ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋራ ራማት ላይ ባደረገው ጦርነት ካቈሰሉት ቍስል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በመቍሰሉም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሆራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ ከቊስሉ ለመፈወስ ተመልሶ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ፤ አካዝያስም ኢዮራምን ለመጠየቅ ወደዚያ ሄደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከሶ​ር​ያም ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ፤ ታም​ሞም ነበ​ርና የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ የአ​ክ​ዓ​ብን ልጅ ኢዮ​ራ​ምን ያይ ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከሶርያም ንጉሥ ከአዛኤል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቍስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፤ ታምሞም ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ያይ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 22:6
8 交叉引用  

ኢዮራምም ከንጉሥ አዛሄል ጋር ሆኖ በሬማት በተደረገው ጦርነት የደረሰበትን ቁስል ለመፈወስ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ተመለሰ። የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በደረሰበት ጉዳት እርሱን ለመጠየቅ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ።


ንጉሥ ኢዮራም ግን የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን ጦርነት በገጠመው ጊዜ፥ ሶርያውያን ካደረሱበት ቊስል ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል ተመልሶ ነበር። ኢዩም፥ “እንግዲህ ሐሳባችሁ እንዲህ ከሆነ፥ ይህን ነገር ወደ ኢይዝራኤል ሄዶ እንዳይናገር፥ ማንም ሰው ከዚህች ከተማ ሾልኮ እንዳይወጣ ጠብቁ” አለ።


ወደ ይሁዳም ወጡ፥ ወረርዋትም፥ የንጉሡንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወንዶች ልጆቹንም ሴቶች ልጆቹንም ማረኩ፤ ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አላስቀሩለትም።


በኢየሩሳሌም የነበሩትም ታናሹን ልጁን አካዝያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡት። የመጣባቸው የዓረብና የአሊማዞን የሽፍቶች ጭፍራ የእርሱን ታላቆች ገድለዋቸው ነበርና። የይሁዳም ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ።


በምክራቸውም ሄደ፥ ከእስራኤልም ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገለዓድ ሊዋጋ ሄደ፤ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቈሰሉት።


አካዝያስም ወደ ኢዮራም በመምጣቱ እዲጠፋ የጌታ ፈቃድ ነበረ፤ በመጣም ጊዜ ከኢዮራም ጋር ጌታ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ ወደ ቀባው ወደ ናሜሲ ልጅ ወደ ኢዩ ወጣ።


ኢይዝራኤል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥


跟着我们:

广告


广告