Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ዜና መዋዕል 11:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሮብዓምም ከሚስቶቹና ከቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ወደደ፤ ዐሥራ ስምንትም ሚስቶችና ስልሳ ቁባቶች ነበሩት፥ ሀያ ስምንት ወንዶችና ስልሳ ሴቶች ልጆች ወለደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሮብዓም መዓካን የአቤሴሎምን ሴት ልጅ ከሌሎቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ይልቅ አብልጦ ወደዳት። በአጠቃላይ ዐሥራ ስምንት ሚስትና ስድሳ ቁባት፣ ሃያ ስምንት ወንድና ስድሳ ሴት ልጆች ነበሩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሮብዓም በጠቅላላ ዐሥራ ስምንት ሚስቶችና ሥልሳ ቊባቶች ነበሩት፤ ከእነርሱም ኻያ ስምንት ወንዶችና ሥልሳ ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ ከሚስቶቹና ከቊባቶቹ ሁሉ የአቤሴሎምን ልጅ ማዕካን አብልጦ ይወድ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሮብ​ዓ​ምም ከሚ​ስ​ቶ​ቹና ከቁ​ባ​ቶቹ ሁሉ ይልቅ የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምን ልጅ መዓ​ካን ወደደ፤ ዐሥራ ስም​ን​ትም ሚስ​ቶ​ችና ስድሳ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት፤ ሃያ ስም​ንት ወን​ዶ​ችና ስድሳ ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሮብዓምም ከሚስቶቹና ከቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ወደደ፤ ዐሥራ ስምንትም ሚስቶችና ስድሳ ቁባቶች ነበሩት፤ ሀያ ስምንት ወንዶችና ስድሳ ሴቶች ልጆች ወለደ።

参见章节 复制




2 ዜና መዋዕል 11:21
11 交叉引用  

እንዲሁም፥ ረኡማ የተባለችው የናኮር ቊባት ደግሞ ጤባሕን፥ ገሐምን፥ ተሐሽንና፥ ማዕካን ወለደችለት።


ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ፥ ከበፊቶቹ በተጨማሪ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ዕቁባቶችን አስቀመጠ፤ ሚስቶችም አገባ፤ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።


ሰሎሞን የነገሥታት ልጆች የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሦስት መቶ ቁባቶች ነበሩት፤ እነርሱም ሰሎሞንን ከጌታ እንዲርቅ አደረጉት።


መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ማዕካ ተብላ የምትጠራ የአቤሴሎም ልጅ ነበረች።


ተጠበበም፥ ልጆቹንም ሁሉ በይሁዳና በብንያም አገር ሁሉ በተመሸጉትም ከተሞች ሁሉ ከፋፈላቸው፤ ብዙም ስንቅ ሰጣቸው፤ ብዙም ሚስቶች ፈለገላቸው።


ልቡ እንዳይስትም ብዙ ሚስቶችን አያግባ፤ ብዙ ብርና ወርቅም አያግበስብስ።


ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፥ የብኩርናን መብት ከማይወዳት ሚስቱ ከወለደው በኩር ልጅ ገፎ፥ ከሚወዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ፥ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤


ብዙ ሚስቶች ስላገባ ሰባ ልጆች ነበሩት፤


跟着我们:

广告


广告