1 ጢሞቴዎስ 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱ በሥጋ ተገለጠ፤ በመንፈስ ጸደቀ፤ በመላእክት ታየ፤ በአሕዛብ ዘንድ ተሰበከ፤ በዓለም ባሉት ታመነ፤ በክብር ዐረገ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ። 参见章节 |