Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ተሰሎንቄ 2:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ወደ እናንተ ልንመጣ ፈልገን ነበርና፤ በእርግጥም እኔ ጳውሎስ አንድና ሁለት ጊዜ ሞክሬ ነበር፥ ሰይጣን ግን መሰናክል ሆነብን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ወደ እናንተ ለመምጣት ፈልገን ነበር፤ በተለይም እኔ ጳውሎስ ብዙ ጊዜ ሞክሬ ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን አዘገየን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ወደ እናንተ መምጣት ፈልገን ነበር፤ በተለይም እኔ ጳውሎስ ወደ እናንተ ለመምጣት ደጋግሜ ሞክሬ ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን ከለከለን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፤ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና፥ እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።

参见章节 复制




1 ተሰሎንቄ 2:18
13 交叉引用  

እግዚአብሔር በአንድም በሁለትም መንገድ ይናገራል፥ ሰው ግን አያስተውለውም።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ “ሂድ አንተ ሰይጣን ‘ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው።


ወንድሞች ሆይ! በሌሎቹ ሕዝቦች እንዳገኘሁት በእናንተም ፍሬ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳቀድሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ እንድታውቁ እወዳለሁ።


ስለዚህ ደግሞ ወደ እናንተ እንዳልመጣ ብዙ ጊዜ ተከለከልሁ።


እኔ ጳውሎስ፥ ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ ጽፌላችኋለሁ።


በተሰሎንቄ እንኳ ሳለሁ፥ ከአንድ ጊዜ በላይ የሚያስፈልገኝን ነገር ልካችሁልኝ ነበርና።


ይህን ሰላምታ እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ ጽፌዋለሁ። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።


እኔ ጳውሎስ በራሴ እጅ ይህን ሰላምታ ጽፌአለሁ፤ ይህ በማንኛውም መልእክቴ ውስጥ የሚገኝ ምልክት ነው፤ እንዲህ እጽፋለሁ።


ይልቁንም እንደዚህ የሆንሁ እኔ ጳውሎስ ሽማግሌው፥ አሁንም ደግሞ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ የሆንሁ፥ ስለ ፍቅር እለምናለሁ።


የሚጠብቅህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያስገባ ነው፤ ለዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።


跟着我们:

广告


广告