Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 26:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታ በቀባው ላይ እጄን ከማንሣት ጌታ ይጠብቀኝ! ነገር ግን በራስጌው አጠገብ ያለውን ጦርና የውሃ መያዣውን ያዝና እንሂድ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ! ነገር ግን በራስጌው አጠገብ ያለውን ጦርና የውሃ መያዣውን ያዝና እንሂድ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር ቀብቶ ባነገሠው ንጉሥ ላይ ጒዳት የማድረስ ተግባርስ ከእኔ ይራቅ! ይልቅስ ጦሩንና ውሃ መቅጃውን ይዘንበት እንሂድ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀ​ባው ላይ እጄን እዘ​ረጋ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው፤ አሁ​ንም በራሱ አጠ​ገብ ያለ​ውን ጦርና የው​ኃ​ውን መን​ቀል ይዘህ እን​ሂድ፤” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እኔ ግን እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፥ አሁንም በራሱ አጠገብ ያለውን ጦርና የውኃውን መንቀል ይዘህ እንሂድ አለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 26:11
11 交叉引用  

ዳዊትም፥ “ታዲያ ጌታ የቀባውን ለማጥፋት እጅህን ስታነሣ እንዴት አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው።


ዳዊትም፥ “ ‘ጌታ የቀባውን ገድያለሁ’ ስትል የገዛ አፍህ መስክሮብሃልና፥ ደምህ በራስህ ላይ ይሁን” አለው።


ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ፥ “ሺምዒ በጌታ የተቀባውን የረገመ ስለሆነ፥ መሞት አይገባውምን?” አለ።


የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፥ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።


ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር አስቡ።


“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።


ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም በረከትን ልትወርሱ ተጠርታችኋል።


እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”


አባቴ ሆይ፤ የልብስህ ቁራጭ ይኸው በእጄ ላይ ተመልከተው! የልብስህን ጫፍ ቆረጥሁ እንጂ አንተን አልገደልኩህም። አሁንም ክፋት ወይም ዐመፅ አለመፈጸሜን ዕወቅልኝ፤ ተረዳልኝም፤ እኔ ክፉ አልሠራሁብህም፤ አንተ ግን ሕይወቴን ለማጥፋት እያሳደድኸኝ ነው።


ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፥ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር።


ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቁረጡ ልቡ በኀዘን ተመታ።


跟着我们:

广告


广告