Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 23:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ስለዚህ የሚደበቅባቸውን ቦታዎች ሁሉ ካያችሁ በኋላ ግልጽ መረጃ ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አብሬችሁ እሄዳለሁ፤ ብቻ በዚያ አገር ይገኝ እንጂ በይሁዳ ነገዶች ሁሉ መካከል ከገባበት ጉድጓድ ገብቼ አወጣዋለሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የሚደበቅባቸውን ቦታዎች ሁሉ ካያችሁ በኋላ ግልጽ መረጃ ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አብሬችሁ እሄዳለሁ፤ ብቻ በዚያ አገር ይገኝ እንጂ በይሁዳ ነገዶች ሁሉ መካከል ከገባበት ጕድጓድ ገብቼ አወጣዋለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የሚሸሸግባቸውን ስፍራዎች በትክክል አግኙ፤ ያገኛችሁትንም ማስረጃ ወዲያው ይዛችሁልኝ ኑ፤ ከዚያም በኋላ እኔ አብሬአችሁ እሄዳለሁ፤ አሁንም በዚያው ግዛት ውስጥ የሚኖር ከሆነ መላውን የይሁዳ ግዛት ማሰስ ቢያስፈልገኝም እንኳ እርሱን በማደን እይዘዋለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከአ​ያ​ችሁ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያ​ችም ምድር ካለ በይ​ሁዳ አእ​ላፍ ሁሉ እፈ​ት​ሻ​ታ​ለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እርሱ የሚደበቅበትንና የሚሸሸግበትን ስፍራ እዩና እወቁ፥ በእርግጥም ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ፥ በምድርም ውስጥ ቢሸሸግ በይሁዳ አእላፋት ሁሉ መካከል እፈልገዋለሁ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 23:23
14 交叉引用  

ንጉሡ አንተን ለማግኘት ፈልጎ በዓለም ላይ መልእክተኛ ያልላከበት አገር እንደሌለ በአምላክህ በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ፤ የአንድ አገር መሪ አንተ በአገሩ ውስጥ አለመኖርክን ባስታወቀው ቍጥር ንጉሥ አክዓብ የአንተን አለመኖር በመሐላ እንዲያረጋግጥለት ጠይቆአል።


የሶርያም ንጉሥ “እርሱ የሚገኝበትን ስፍራ ፈልጉ፤ እኔም ልኬ እማርከዋለሁ” አላቸው። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ በዶታን የሚኖር መሆኑ ተነገረው፤


በመንደሮች ሸምቆ ይቀመጣል ንጹሓንን በስውር ይገድል ዘንድ፥ ዐይኖቹም ወደ ምስኪኑ ይመለከታሉ።


እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።


ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ከዚህ በኋላ የቀሩት ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።


ባረፈም ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት ወደ እስራኤል ልጆች ተመለስ።”


የፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ሲቀረው፥ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ኢየሱስን የሚይዙበትና የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።


አሁንም ሂዱና አጣሩ ዘወትር የት እንደ ሆነና በዚያ ያየውን ሰው ለይታችሁ ዕወቁ፤ እጅግ ተንኰለኛ መሆኑን ሰምቻለሁ።


ሰዎቹም ሳኦል ከመሄዱ በፊት ወደ ዚፍ ተመለሱ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ከየሴሞን በስተ ደቡብ በዓረባ ውስጥ ባለው በማዖን ምድረ በዳ ነበሩ።


በዛሬው ዕለት በዋሻው ውስጥ ጌታ አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ላይ እንደጣለህ እነሆ በገዛ ዓይንህ አይተሃል፤ አንዳንዶች እንድገድልህ ገፋፍተውኝ ነበር፤ እኔ ግን፥ ‘ጌታ በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ በማለት ራራሁልህ።


跟着我们:

广告


广告