Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 23:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የቅዒላ ሰዎች አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ባርያህ እንደሰማውም ሳኦል ወደዚህ ይወርድ ይሆን? የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፤ ለአገልጋይህ እንድትነግረው እለምንሃለሁ።” ጌታም፥ “አዎን ይወርዳል” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የቅዒላ ገዦች አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ባሪያህ እንደሰማውም ሳኦል ወደዚህ ይወርድ ይሆን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለባሪያህ እንድትነግረው እለምንሃለሁ።” እግዚአብሔርም፣ “አዎን ይወርዳል” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ታዲያ፥ የቀዒላ ከተማ ነዋሪዎች እኔን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ሳኦልስ እኔ እንደ ሰማሁት ወደዚህ መምጣቱ እውነት ነውን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! መልስ እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ!” እግዚአብሔርም “አዎ፥ ሳኦል በእርግጥ ይመጣል” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የቂ​አላ ሰዎ​ችስ ይከ​በ​ባ​ሉን? ባሪ​ያ​ህስ እንደ ሰማ ሳኦል በውኑ ይወ​ር​ዳ​ልን? የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! ለባ​ር​ያህ ንገ​ረው” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይወ​ር​ዳል” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የቅዒላ ሰዎች በእጁ አሳልፈው ይሰጡኛልን? ባሪያህስ እንደ ሰማ ሳኦል በውኑ ይወርዳልን? የእስራኤል አምላክ አቤቱ፥ እንድትነግረኝ እለምንሃለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ ይወርዳል አለ።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 23:11
6 交叉引用  

በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።


ጌታም አስታወቀኝ እኔም አወቅሁ፤ ሥራቸውንም ገለጥህልኝ።


ወደ እኔ ተጣራ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቃቸውን ታላላቅና ስውር የሆኑ ነገሮችን እነግርሃለሁ።


ከዚያም ዳዊት እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፤ ሳኦል ወደ ቅዒላ መጥቶ፥ በእኔ ምክንያት ከተማዪቱን ለማጥፋት ማሰቡን ባርያህ በትክክል ሰምቷል።


ዳዊትም፥ “የቅዒላ ነዋሪዎች እኔንና ሰዎቼን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡናል?” ሲል ጠየቀ። ጌታም፥ “አዎን አሳልፈው ይሰጧችኋል” አለው።


跟着我们:

广告


广告