Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ሳሙኤል 12:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጌታን የማትሰሙና የማትታዘዙ፥ በትእዛዛቱም ላይ የምታምጹ ከሆነ ግን፥ እጁ በአባቶቻችሁ ላይ እንደ ነበረች ሁሉ በእናንተም ላይ ትሆናለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እግዚአብሔርን የማትታዘዙና በትእዛዞቹም ላይ የምታምፁ ከሆነ ግን፣ እጁ በአባቶቻችሁ ላይ እንደ ነበረች ሁሉ በእናንተም ላይ ትሆናለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባታዳምጡ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር ቅጣት ይበረታባችኋል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ላይ ብታ​ምፁ፥ በእ​ና​ን​ተና በን​ጉ​ሣ​ችሁ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትመ​ጣ​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ፥ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር እጅ ትሆናለች።

参见章节 复制




1 ሳሙኤል 12:15
12 交叉引用  

አሳንም ሊያገኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ እናንተ ከጌታ ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተውት ግን ይተዋችኋል።


እምቢ ብላችሁ ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል።” የጌታ አፍ ይህን ተናግሮአልና።


በደለኞች ወዮላቸው፤ ጥፋት ይመጣባቸዋል፤


ጻዴ። በአፉ ነገር ላይ ዓመጽ አድርጌአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ እባካችሁ፥ ስሙ መከራዬንም ተመልከቱ፥ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ ተማርከው ሄዱ።


እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፥ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በጌታ ላይ ዐምፃችኋል፥ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?


ጌታን ትታችሁ እንግዶችን አማልክት ብታመልኩ፥ መልካም ካደረገላችሁ በኋላ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፥ ያጠፋችኋልም።”


እስራኤላውያን ለውጊያ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ አስቀድሞ በእነርሱ ላይ እንደተናገረውና እንደማለው እንዲሸነፉ የጌታ እጅ ትከፋባቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እጅግ ተጨነቁ።


እነርሱ ግን አምላካቸውን ጌታን ረሱት፤ ስለዚህ ለሓጾር የጦር አዛዥ ለሲሣራ፥ ለፍልስጥኤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ሰጣቸው።


ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱትም በኋላ የጌታ እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በእባጭ መቅሠፍት መታ።


跟着我们:

广告


广告