Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 9:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን እነዚህን እስከ ዛሬ እንደሚደረገው ሁሉ፥ ሰሎሞን ለግዳጅ ሥራ መለመላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን የእነዚህን ሕዝቦች ዘሮች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚደረገው የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ ያል​ቻ​ሉ​ትን፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ሰሎ​ሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባ​ሮች አድ​ርጎ መለ​መ​ላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ በኋላቸው የቀሩትን ልጆቻቸውን፥ ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 9:21
23 交叉引用  

ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል ሠላሳ ሺህ የግዳጅ ሠራተኞችን መለመለ።


ለሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ የኢየሩሳሌምን ቅጽር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ ሞልተው ያስተካከሉለት የጉልበት ሥራ ለመሥራት የሚገደዱ ሠራተኞች ነበሩ፤ እንዲሁም ሐጾር፥ መጊዶና ጌዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችንም እንዲሠሩለት አደረገ።


ከእስራኤል ሕዝብ ያልሆኑትን ከአሞራውያን፥ ከኬጢያውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከኤው ያውንና ከኢያቡሳውያን ሕዝቦች ሁሉ የተረፉትን፥


ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች እንዲሰበስቡ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች እንዲወቅሩ ጠራቢዎችን አኖረ።


የእስራኤልም ልጆች ያላጠፉአቸውን፥ በኋላቸው በምድሪቱ ላይ የቀሩትን ልጆቻቸውን ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።


በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃው መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዱ በየርስቱና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ኖሩ።


የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፕሪዳ ልጆች፥


የትጉ እጅ ትገዛለች፥ የታካች እጅ ግን ትገብራለች።


ከተቀበሉህና ደጃቸውን ከከፈቱልህ በከተማዋ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ ገባርህ ይሁን፤ ያገልግልህም።


በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።


በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ እነርሱም የጉልበት ሥራ የሚሠሩ ባሮች ሆነዋል።


የምናሴ ልጆች ግን የእነዚህን ከተሞች ሰዎች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያ አገር በመቀመጥ ጸኑ።


የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም።


ነገር ግን የብንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ከዚያ አላስወጧቸውም፤ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከብንያማውያን ጋር በዚያ አብረው ይኖራሉ።


የአሞራውያን ድንበር አቅራቢያም መተላለፊያ እስከ ሴላዕና ከዚያም የሚያልፍ ነበር።


ስለዚህ ጌታ በእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እንዲህም አለ፤ “ይህ ሕዝብ ለቀደሙ አባቶቹ የሰጠሁትን ቃል ኪዳን ስለተላለፈ፥ እኔንም ስላልሰማ፥


በዚህ ጊዜ በከነዓን ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተሳትፈው የማያውቁትን እስራኤላውያን ለመፈተን፥ ጌታ ባሉበት የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告