Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 8:60 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

60 በዚህ ዓይነት የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ መሆኑንና ያለ እርሱም ሌላ አምላክ አለመኖሩን ያውቃሉ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

60 ይኸውም የምድር ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ እንደ ሆነና ከርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

60 በዚህ ዐይነት የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ መሆኑንና ያለ እርሱም ሌላ አምላክ አለመኖሩን ያውቃሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

60 የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ከእ​ር​ሱም በቀር ሌላ እንደ ሌለ ያውቁ ዘንድ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

60 የምድር አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ከእርሱም በቀር ሌላ እንደሌለ ያውቅ ዘንድ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 8:60
17 交叉引用  

ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ “ጌታ አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው!” አሉ።


አንተ ጸሎቱን ስማ፤ ሕዝብህ እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች አንተን በማወቅ እንዲታዘዙህና እንዲያከብሩህ አድርግ፤ በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ የዚህን ሰው ጸሎት ስማ፤ እንድታደርግለት የሚለምንህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ይህ እኔ የሠራሁት ቤተ መቅደስ የአንተ ስም የሚጠራበት መሆኑን ያውቃሉ።


የእኔ ያገልጋዩና የሕዝቡ የእስራኤል የየዕለት ፍላጎት ይሟላ ዘንድ እነዚህ ለእግዚአብሔር ያቀረብኳቸው ልመናዎች ቀንና ሌሊት ወደ እግዚአብሔር አምላክ ይቅረቡ።


እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም መንግሥታት ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦር ንጉሥ በመታደግ አድነን።”


ለእኔ ሕዝብ አድርጌ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብጽ ጭቆና ያወጣኋችሁ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


እንግዲህም አምላካችን ጌታ ሆይ፥ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ ጌታ እንደሆንህ እንዲያውቁ ከእጁ አድነን።”


ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ ጌታ እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?


የእስራኤል ንጉሥ ጌታ፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ፥ እኔ ፍጻሜም ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።


አትፍሩ አትደንግጡም፤ ከጥንቱም ጀምሬ አልነገርኋችሁም? ወይስ አላሳየኋችሁም? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ሌላ ዐለት የለም፤ አንድም አላውቅም።


እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።


እኔም በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔም ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፥ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም።


ጌታም አምላካችሁ እንደሆነ እንድታውቁ ይህ ለእናንተ ተገልጧል፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም።


እንግዲህ፥ ጌታ በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቁ፥ በልባችሁም ያዙት።


ይኸውም የጌታ እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ፥ አምላካችሁንም ጌታን ለዘለዓለሙ እንድትፈሩ ነው።”


ጌታ ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቆርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ እግዚአብሔር መኖሩን ያውቃል።


跟着我们:

广告


广告