1 ነገሥት 3:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ሁለተኛይቱ ሴት ግን፥ “አይደለም! በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!” አለች። የመጀመሪያይቱ ሴት “አይደለም! የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው!” አለች። በዚህም ዓይነት በንጉሡ ፊት ተከራከሩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ሌላዪቱም ሴት፣ “ነገሩ አንቺ እንደምትዪው አይደለም፤ የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለውም የእኔ ነው” አለች። የመጀመሪያዋ ሴት ግን አጠንክራ፣ “አይደለም! የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው” አለች፤ በዚህ ሁኔታም በንጉሡ ፊት ተከራከሩ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ሁለተኛይቱ ሴት ግን፥ “አይደለም! በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፤ የሞተው ግን የአንቺ ነው!” አለች። የመጀመሪያይቱ ሴት “አይደለም! የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው!” አለች። በዚህም ዐይነት በንጉሡ ፊት ተከራከሩ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ሁለተኛዪቱም ሴት፥ “አይደለም ደኅነኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞተው የአንቺ ልጅ ነው እንጂ አለች።” እንዲሁም በንጉሡ ፊት ይነጋገሩ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ሁለተኛይቱም ሴት “ደኅነኛው የኔ ልጅ ነው፤ የሞተውም የአንቺ ልጅ ነው እንጂ አንቺ እንደምትዪው አይደለም፤” አለች። ይህችም “የሞተው የአንቺ ልጅ ነው፤ ደኅነኛውም የእኔ ልጅ ነው፤” አለች፤ እንዲሁም በንጉሡ ፊት ይነጋገሩ ነበር። 参见章节 |