Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 2:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ኢዮአብ ወደ ጌታ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መሆኑን ንጉሥ ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን፣ “ሂድና ግደለው!” ብሎ አዘዘው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ኢዮአብ ወደ ተቀደሰ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ኢዮ​አብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ኳን ሸሽቶ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ እንደ ያዘ ሰማ፤ ንጉሥ ሰሎ​ሞ​ንም ወደ ኢዮ​አብ እን​ዲህ ሲል ላከ፤ “በመ​ሠ​ዊ​ያው ቀንድ የተ​ማ​ጠ​ንህ ምን ሆነህ ነው?” ኢዮ​አ​ብም፥ “ፈር​ቼ​ሃ​ለ​ሁና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ጠ​ንሁ” አለ። ሰሎ​ሞ​ንም የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን ልኮ፥ “ሂድ ግደ​ልና ቅበ​ረው” ብሎ አዘ​ዘው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ንጉሡም ሰሎሞን ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሠዊያውን እንደ ያዘ ሰማ፤ ሰሎሞንም የዮዳሄን ልጅ በናያስን “ሂድ፤ ውደቅበት፤” ብሎ አዘዘው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 2:29
9 交叉引用  

የዮዳሔ ልጅ በናያ የከሪታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፥ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ አማካሪዎች ነበሩ።


ስለዚህም አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ አዶንያስን ገደለው።


እርሱም ወደ ጌታ ድንኳን ሄዶ ኢዮአብን “ከዚህ ድንኳን እንድትወጣ ንጉሡ አዞሃል” አለው። ኢዮአብ ግን “አልወጣም! እዚሁ እሞታለሁ!” አለ። በናያም ተመልሶ ኢዮአብ ያለውን ለንጉሡ ነገረው።


ሰሎሞንም በናያን እንዲህ አለው፤ “ኢዮአብ እንዳለህ ግደለውና ቅበረው፤ በዚህ አኳኋን ኢዮአብ ካፈሰሰው ንጹሕ ደም በደል የእኔንና የአባቴን ቤት የነጻን አድርገን።


ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ።


ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውንም በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲገደል ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው።


የሰው ደም ያለበት ሰው እስከጉድጓድ ይሸሻል፥ ማንም አያስጠጋውም።


ሽማግሌ፥ ወጣት፥ ድንግል፥ ሕፃናትንና ሴቶችን ግደሉ፥ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፥ በመቅደሴም ጀምሩ። በቤቱ ፊት ለፊት ከነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።


ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአል፤ በቅድሚያም በእኛ የሚጀመር ከሆነ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?


跟着我们:

广告


广告