Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 11:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሀዳድ በግብጽ ሳለ የንጉሥ ዳዊትንና የሠራዊቱን አዛዥ የኢዮአብን መሞት በሰማ ጊዜ “ወደ አገሬ ተመልሼ እንድሄድ አሰናብተኝ” ሲል ንጉሡን ጠየቀ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሃዳድ በግብጽ ሳለ ዳዊት ከአባቶቹ ጋራ ማንቀላፋቱን፣ የሰራዊቱ አዛዥ ኢዮአብም መሞቱን ሰማ። ሃዳድም ፈርዖንን፣ “ወደ አገሬ እንድመለስ አሰናብተኝ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሀዳድ በግብጽ ሳለ የንጉሥ ዳዊትንና የሠራዊቱን አዛዥ የኢዮአብን መሞት በሰማ ጊዜ “ወደ አገሬ ተመልሼ እንድሄድ አሰናብተኝ” ሲል ንጉሡን ጠየቀ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አዴ​ርም በግ​ብፅ ሳለ ዳዊት እንደ አባ​ቶቹ እን​ዳ​ን​ቀ​ላፋ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ አዴር ፈር​ዖ​ንን፥ “ወደ ሀገሬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ተኝ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሃዳድም በግብጽ ሳለ ዳዊት ከአባቶቹ ጋር እንዳንቀላፋ፥ የሠራዊቱም አለቃ ኢዮአብ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ ሃዳድ ፈርዖንን “ወደ አገሬ እሄድ ዘንድ አሰናብተኝ፤” አለው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 11:21
10 交叉引用  

ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹን አሰናበታቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ “በመንገድ እርስ በርሳችሁ አትጣሉ።”


ከዚያም አበኔር ዳዊትን፥ “ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ልሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።


እርሷም ገኑባት ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ እርሱንም ንግሥቲቱ ወስዳ በቤተ መንግሥት አሳደገችው፤ ከንጉሡም ወንዶች ልጆች ጋር አብሮ ኖረ።


ንጉሡም “ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ ያሰብከው ከቶ ምን ጎድሎብህ ነው?” አለው። ሀዳድም “ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ” ሲል ለንጉሡ መለሰ፤


ዳዊት ሞተ፤ የእርሱ ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌምም ተቀበረ።


ስለዚህ በናያ በታዘዘው መሠረት ኢዮአብን ገደለው፤ በቤቱም አጠገብ በሚገኘው በረሓ ተቀበረ።


ጌታም ሙሴን በምድያን፦ “ወደ ግብጽ ተመልሰህ ሂድ ነፍስህን የሚፈልጓት ሰዎች ሁሉ ሞተዋልና” አለው።


እንዲህም አለው፦ “ተነሣ፤የሕፃኑን ነፍስ የሚፈልጉት ሞተዋልና ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ምድር ሂድ።”


እርሷም እንዲህ አለች፦ “እንደ ቃላችሁ ይሁን፤” ከዚያም በኋላ በደኅና አሰናበተቻቸው እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው።


በነጋም ጊዜ በማለዳ ሳሙኤል ሳኦልን ከሰገነቱ ላይ ጠርቶ፥ “ላሰናብትህ ስለሆነ ተዘጋጅ” አለው። ሳኦልም ተዘጋጅቶ እንዳበቃ፥ ከሳሙኤል ጋር ተያይዘው ወደ ውጭ ወጡ።


跟着我们:

广告


广告