Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 1:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 አዶንያስም ሰሎሞንን ፈራ፥ ተነሥቶም ሄደ፥ የመሠዊያውንም ቀንድ ያዘ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 አዶንያስ ግን ሰሎሞንን በመፍራት ሄዶ፣ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 አዶንያስም ሰሎሞንን ስለ ፈራ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄዶ የመሠዊያውን ቀንዶች በመያዝ ተማጠነ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 አዶ​ን​ያ​ስም ከሰ​ሎ​ሞን ፊት የተ​ነሣ ፈራ፤ ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀንድ ያዘ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 አዶንያስም ሰሎሞንን ፈራ፤ ተነሥቶም ሄደ፤ የመሠዊያውንም ቀንድ ያዘ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 1:50
9 交叉引用  

አዶንያስም የጠራቸው ሁሉ ፈሩ፥ ተነሥተውም እያንዳንዳቸው በየመንገዳቸው ሄዱ።


ለሰሎሞንም፦ “እነሆ፥ አዶንያስ ንጉሡን ሰሎሞንን ፈርቶ፦ ‘ንጉሡ ሰሎሞን ባርያውን በሰይፍ እንዳይገድለኝ ዛሬ ይማልልኝ’ ብሎ የመሠዊያውን ቀንድ ይዞአል” አሉት።


በአንድ በኩል የአዶንያስ ደጋፊ፥ በሌላ በኩል ደግሞ የአቤሴሎም ተቃዋሚ የሆነው ኢዮአብ የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ጌታ ድንኳን ሄደ፤ በዚያም የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ተማጠነ።


ጌታ አምላክ ነው፥ ለእኛም አበራልን፥ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ፥ ቅርንጫፎች ይዘን፥ ለበዓሉ ዑደት እናድርግ


ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውንም በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲገደል ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው።


በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አድርግለት፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ፤ በነሐስም ለብጠው።


አሮን በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል፤ በዓመት አንድ ጊዜ ለትውልዳችሁ ማስተስረያ በሚሆን በኃጢአት መሥዋዕት ደም ማስተስረያ ያደርግበታል። ለጌታ እጅግ የተቀደሰ ነው።


በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አደረገበት፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ በነሐስም ለበጠው።


የመሠዊያው ምድጃው አራት ክንድ ነው፤ ከመሠዊያው ምድጃ በላይ አራት ቀንዶች አሉ።


跟着我们:

广告


广告