Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከዚችም ዓለም ገዢዎች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ፥ አላወቀም፤ ዐውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚህ ዓለም ገዦች አንዳቸውም ይህን ጥበብ አልተረዱትም፤ ቢረዱትማ ኖሮ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ ዓለም ገዢዎች መካከል ይህን ጥበብ ያወቀ ማንም የለም፤ ዐውቀውትስ ቢሆን ኖሮ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የዚህ ዓለም ሹሞ​ችም አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ይህ​ንስ ቢያ​ውቁ ኑሮ የክ​ብር ባለ​ቤ​ትን ባል​ሰ​ቀ​ሉ​ትም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 2:8
22 交叉引用  

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “የሰማያትና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


በእሾህ መካከል የተዘራው፥ ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ጭንቀትና የሃብት ማታለል ቃሉን ያንቃል፤ የማያፈራም ይሆናል።


ኢየሱስም “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፤” አለ። ልብሱንም ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉት።


ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው።


ከአለቆች ወይም ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለን?


ስለዚህም “አባትህ ወዴት ነው?” አሉት። ኢየሱስ መልሶ “እኔንም ሆነ አባቴንም አታውቁም፤ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ደግሞ ባወቃችሁ ነበር፤” አላቸው።


በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤


እርሱም እንዲህ አለ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ! ስሙ። የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም በካራን ሳይቀመጥ ገና በመስጴጦምያ ሳለ ታየና


ጥበበኛ የት አለ? ጻፊስ የት አለ? የዚህ ዘመን ተከራካሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?


በዐዋቂዎች መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የዚህን ዓለም ወይም መጨረሻቸው ጥፋት የሚሆነውን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም፤


ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወገድ እስከ ዛሬ ድረስ በመኖሩና፥ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና፥ አሳባቸው ደነዘዘ።


የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።


እነርሱ ባለማወቃቸውና በልባቸው ደንዳንነት ምክንያት፥ ልቡናቸው ጨለመ፤ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤


ይሁንና ከዚህ ቀደም ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም የነበርኩ ብሆንም እንኳ ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምሕረትን አገኘሁ፤


ወንድሞቼ ሆይ! ክቡር በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የምታምኑ በመሆናችሁ፥ አድልዎን አታድርጉ።


跟着我们:

广告


广告