Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 9:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ከወንድሞቻቸውም ከቀዓታውያን አንዳንዶቹን በየሰንበቱ የተቀደሰውን ኅብስት እንዲያዘጋጁ ሹሞች ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በየሰንበቱ ለሚዘጋጀው ገጸ ኅብስትም ኀላፊነቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 የቀዓት ጐሣ አባሎች አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደስ የሚሆን ኅብስት በየሰንበቱ የማዘጋጀት ኀላፊነት ነበረባቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 በየ​ሰ​ን​በ​ቱም ያዘ​ጋጁ ዘንድ ቀዓ​ታ​ዊው በን​ያ​ስና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው በገጹ ኅብ​ስት ላይ ሹሞች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 የበሰንበቱም ያዘጋጁ ዘንድ ከወንድሞቻቸው ከቀዓታውያን አንዳንዱ በገጹ ኅብስት ላይ ሹሞች ነበሩ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 9:32
5 交叉引用  

በገበታው ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።


በቀዓት ውስጥም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ይካተቱ ነበር፤ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።


ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ካህናት ብቻ እንጂ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሊበሉት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕቱን ኅብስት በላ።


跟着我们:

广告


广告