Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 28:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ዳዊትም ለመቅደሱ ወለል፥ ለቤቱም፥ ለቤተ መዛግብቱም፥ ለደርቡና ለውስጡም ጓዳዎች፥ ለስርየቱም መክደኛ መቀመጫ ንድፈ ሐሳቡን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚያም ዳዊት የቤተ መቅደሱን መመላለሻ፣ የሕንጻውን፣ የዕቃ ቤቶቹን፣ የፎቁንና የውስጥ ክፍሎቹን እንዲሁም የማስተስረያውን ቦታ ንድፍ ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞን የቤተ መቅደሱን የዕቃ ግምጃ ቤቶቹን፥ በደርቡና በምድር ቤቱ የሚገኙትን ክፍሎችና ኃጢአት የሚሰረይበትን የቅድስተ ቅዱሳኑን አሠራር የሚገልጥ ዕቅድ ሰጠው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ዳዊ​ትም ለመ​ቅ​ደሱ ወለል፥ ለቤ​ቱም፥ ለቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም፥ ለደ​ር​ቡና ለው​ስ​ጡም ጓዳ​ዎች፥ ለስ​ር​የ​ቱም መክ​ደኛ መቀ​መጫ ምሳ​ሌ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ዳዊትም ለመቅደሱ ወለል፥ ለቤቱም፥ ለቤተ መዛግብቱም፥ ለደርቡና ለውስጡም ጓዳዎች፥ ለስርየቱም መክደኛ መቀመጫ ምሳሌውን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 28:11
28 交叉引用  

የእያንዳንዱ ፎቅ ቁመት ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ሆኖ ከውጪ በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ተጠግቶ የተሠራው ባለ ሦስት ፎቅ ተጨማሪ ሕንጻ ከዋናው ሕንጻዎች ከሊባኖስ ዛፍ በተሠሩት አግዳሚ ሠረገሎች የተያያዘ ነበር።


በመግቢያው በር የሚገኘው በረንዳ ቁመቱ አራት ሜትር ተኩል፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ዘጠኝ ሜትር ነበር።


ደግሞም ለጌታ ቤት አደባባዮችና በዙሪያው ለሚሆኑ ጓዳዎች፥ ለእግዚአብሔርም ቤት ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት፥ ለንዋየ ቅድሳቱም ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት በመንፈሱ ያሰበውን ንድፈ ሐሳብ ሁሉ ሰጠው።


ዳዊትም፦ “የሥራውን ሁሉ ንድፈ ሐሳብ እንዳውቅ ይህ ሁሉ በጌታ እጅ ተጽፎ መጣልኝ” አለ።


ካህናቱም የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቱ አምጥተው በመቅደሱ በውስጠኛው ክፍል በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ከኪሩቤል ክንፍ በታች በነበረው በስፍራው አኖሩት።


ትልቅ ለሌዋውያን፥ ለመዘምራን፥ ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቁርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን የማንሣት ቁርባን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቁን ጓዳ አዘጋጅቶለት ነበር።


በተራራው ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ለመስራት ጥንቃቄ አድርግ።”


እኔ እንዳሳየሁህ ሁሉ፥ እንደ ድንኳኑ ምሳሌ፥ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት።


ማደሪያውንም በተራራ እንዳሳየሁህ ምሳሌ አቁም።


“ወደ ሬካባውያን ቤት ሂድና አነጋግራቸው፥ ወደ ጌታም ቤት ከጓዳዎቹ ወደ አንዱ አስገባቸው የወይን ጠጅም እንዲጠጡ ስጣቸው።”


ከበሩ መግቢያ ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው የበሩ መተላለፊያ መጨረሻ ድረስ አምሳ ክንድ ነበረ።


ዐይኑንም አንሥቶ በምጽዋት መቀበያ መባቸውን የሚያስቀምጡ ሀብታሞችን አየ።


ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ በነበረ ጊዜ፥ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ፤” ብሎት ነበርና፤ እነርሱ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ።


跟着我们:

广告


广告