Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 2:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ጌሹርና አራምም የኢያዕርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስልሳውን ከተሞች ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ይሁን እንጂ ጌሹርና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ስድሳ መንደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ነገር ግን የገሹርና የአራም ነገሥታት ሥልሳ የሚያኽሉ ታናናሽ ከተሞችን ከዚያው ከገለዓድ ድል አድርጎ ያዘ፤ ይህም የያኢርንና የቀናትን መንደሮች እንዲሁም በአቅራቢያቸው ያሉትንም ታናናሽ ከተሞች የሚያጠቃልል ነበር፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ናቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ኤስ​ሮ​ምም ጌሱ​ር​ንና አራ​ምን የኢ​ያ​ዔ​ርን ከተ​ሞች ከቄ​ና​ትና ከመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ ጋር ስድ​ሳ​ውን ከተ​ሞች ወሰደ። እነ​ዚህ ሁሉ የገ​ለ​ዓድ አባት የማ​ኪር ልጆች ከተ​ሞች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ጌሹርና አራምም የኢያዕርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስድሳውን ከተሞች ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ነበሩ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 2:23
9 交叉引用  

የኤፍሬምንም ልጆችና የልጅ ልጆች እስከሚያይ ድረስ ቈየ፤ ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች እንደ ልጆቹ አድርጎ ተቀበላቸው።


አቤሴሎም ሸሽቶ ወደ ገሹር ከሄደ በኋላ፥ በዚያ ሦስት ዓመት ተቀመጠ።


በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ፥ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የያኢር ጐሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፥ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት፥ እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጽር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስድሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ።


ሠጉብም በገለዓድ ምድር ሀያ ሦስት ከተሞች ነበሩትን ጌሹርን ወለደ።


ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።


የምናሴ ልጅ ያኢር፥ ባሳንን እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ፥ የአርጎብን ግዛት ሁሉ ወሰደ፥ ይችንም የባሳን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ በሚጠራበት የያኢር መንደሮች ብሎ ጠራ።


የእስራኤል ልጆች ግን ጌሹራውያንንና ማዕካታውያንን አላስወጡም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ጌሹርና ማዕካት በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።


ግዛታቸውም ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥


跟着我们:

广告


广告