Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 19:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሠላሳ ሁለትም ሺህ ሰረገሎች የመዓካንም ንጉሥ ሠራዊት ቀጠሩ፤ መጥተውም በሜድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአሞንም ልጆች ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ወደ ውግያ መጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም ሠላሳ ሁለት ሺሕ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥና ወታደሮች በገንዘብ ቀጠሩ፤ እነርሱም መጥተው በሜድባ አጠገብ ሲሰፍሩ፣ አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት ወጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የተከራዩአቸው ሠላሳ ሁለት ሺህ ሠረገሎችና የንጉሥ ማዕካ ሠራዊት መጥተው በሜዳባ አጠገብ ሰፈሩ፤ ዐሞናውያንም ከየከተሞቻቸው ወጥተው ለጦርነት ተዘጋጁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሠላሳ ሁለ​ትም ሺህ ሰረ​ገ​ሎ​ችን የሞ​ዓ​ካን ንጉ​ሥና ሕዝ​ቡ​ንም ቀጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም በሜ​ድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአ​ሞ​ንም ልጆች ከየ​ከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ሰልፍ መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሠላሳ ሁለትም ሺህ ሠረገሎች የመዓካንም ንጉሥ ሕዝቡንም ቀጠሩ፤ መጥተውም በሜድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአሞንም ልጆች ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ወደ ሰልፍ መጡ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 19:7
12 交叉引用  

አሞናውያን፥ ዳዊት እንደጠላቸው ባወቁ ጊዜ፥ ከቤትረሖብና ከጾባ ሃያ ሺህ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም ንጉሥ መዓካን ከአንድ ሺህ ሰዎቹ ጋር ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ።


ዳዊትም ከእርሱ አንድ ሺህ ሰረገሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረሰኞች፥ ሀያ ሺህም እግረኞች ወሰደ፤ ዳዊትም ለመቶ ሰረገሎች የሚሆኑትን ብቻ አስቀርቶ የሰረገሎቹን ፈረሶች ቋንጃ ቆረጠ።


ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብንና የኃያላኑን ሠራዊት ሁሉ ላከ።


ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ወጣባቸው፤ ወደ መሪሳም መጣ።


ግብፃውያንም የፈርዖን ፈረሶችና ሰረገሎች ፈረሰኞቹም ሠራዊቱም ሁሉ፥ አሳደዱአቸው፤ በባሕሩ በበዓልጽፎን ፊት ለፊት ባለው በፒሃሒሮት ሰፍረው አገኙአቸው።


ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቷል።


ቀስትን ወረወርንባቸው፤ ከሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፉ፤ እሳቱ እስከ ሜድባ እስኪዛመት ድረስ ደመሰስናቸው።”


ግዛታቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥ የሜድባ ሜዳ ሁሉ፥


በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር፥ በሸለቆውም መካከል ካለችው ከተማ ጀምሮ የሜድባን ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥


እርሱም ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎች ስለ ነበሩት እስራኤላውያንን ሃያ ዓመት እጅግ አስጨነቃቸው፤ እነርሱም ይረዳቸው ዘንድ ወደ ጌታ ጮኹ።


ፍልስጥኤማውያን ሠላሳ ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ፈረሰኞች ቁጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ።


跟着我们:

广告


广告