Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 19:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም በሶርያውያን ላይ ለውግያ በተሰለፈ ጊዜ እነርሱ ከእርሱ ጋር ተዋጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ወደ ፊት በመገሥገሥም ከፊት ለፊታቸው የውጊያ መሥመሩን ያዘ። ዳዊትም ሶርያውያንን ጦርነት ለመግጠም ወታደሮቹን አሰለፈ፤ እነርሱም ተዋጉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዳዊት ስለዚህ ነገር በሰማ ጊዜ የእስራኤላውያንን የጦር ኀይል ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ የውጊያ መስመሩን ያዘ፤ ሶርያውያንም እንደዚሁ ቦታቸውን ይዘው ከዳዊት ጋር ጦርነት ገጠሙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዳዊ​ትም በተ​ነ​ገ​ረው ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግሮ መጣ​ባ​ቸው፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ርሱ ጋር ተዋጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፤ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም በሶርያውያን ላይ በተሰለፈ ጊዜ እነርሱ ከእርሱ ጋር ተዋጉ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 19:17
5 交叉引用  

ለዳዊት ይህ በተነገረው ጊዜ፥ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ። ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤


ሶርያውያንም በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ መልእክተኞች ልከው በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን አስመጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሾፋክ በፊታቸው ነበረ።


ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት ሺህ ሰረገለኞች፥ አርባ ሺህም እግረኞች ገደለ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ሾፋክን ገደለ።


የአሞንም ልጆች ወጥተው በከተማይቱ በር አጠገብ ለውግያ ተሰለፉ፤ የመጡትም ነገሥታት ለብቻቸው በሜዳው ላይ ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告