Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 18:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በኤዶምያስም የጦር ሠራዊት አሰፈረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል አድራጊ አደረገው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርሱም በኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በመላው የኤዶም ግዛት ውስጥ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሁሉ ስፍራ ድል አድራጊ አደረገው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በዚ​ያም ሸለቆ ምሽግ ሠርቶ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በኤዶምያስም ጭፍሮች አኖረ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ። እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል ይሰጠው ነበር።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 18:13
19 交叉引用  

ጌታም እንዲህ አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ወገኖች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንዱም ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል።”


አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ፥ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፥ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩክ ይሁን።”


ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው፦ “እነሆ፥ ጌታህ አደረግሁት፥ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት፥ በእህልም በወይንም አበረታሁት፥ ለአንተ ግን፥ ልጄ ሆይ፥ ምን ላድርግ?”


በሰይፍህም ትኖራለህ፥ ለወንድምህም ትገዛለህ፥ ነገር ግን በተቃወምኸው ጊዜ ቀንበሩን ከአንገትህ ትጥላለህ።”


በዚያ ጊዜ ዳዊት በምሽግ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሠራዊት በቤተልሔም ነበረ፤


ዳዊት ከኤዶማውያን ጋር ይዋጋ በነበረ ጊዜ የጦር አዛዡ ኢዮአብ የሞቱትን ለመቅበር ወጥቶ የኤዶማውያንን ወንዶች ልጆች ሁሉ ፈጅቶ ነበር።


ደግሞ የጽሩያ ልጅ አቢሳ ከኤዶማውያን በጨው ሸለቆ ውስጥ ዐሥራ ስምንት ሽህ ሰዎች ገደለ።


ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍርድንና ጽድቅን አደረገላቸው።


ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ የጦር ሠራዊት አሰፈረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል አድራጊ አደረገው።


ጌታ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።


ለነገሥታት መድኃኒትን የሚሰጥ፥ ባርያውን ዳዊትን ከክፉ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።


ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል።


በደማስቆ አርስጦስዮስ ከተባለ ንጉሥ በታች የሆነ የሕዝብ ገዥ ሊይዘኝ ፈልጎ የደማስቆ ሰዎችን በከተማው አሰማርቶ ነበር፤


ከዚያ በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጦር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ጊብዓ ትሄዳለህ። ወደ ከተማዪቱ እንደ ደረስክም የነቢያት ጉባኤ በበገና፥ በከበሮ፥ በዋሽንትና በመሰንቆ ታጅበው ትንቢት እየተናገሩ ከማምለኪያው ኰረብታ ላይ ሲወርዱ ታገኛቸዋለህ።


ዮናታን ጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፥ “ዕብራውያን ይስሙት!” በማለት በሀገሩ ሁሉ መለከት አስነፋ።


አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና በሌላ በኩል ወዳለው የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ይህን ግን ለአባቱ አልነገረውም ነበር።


ጌታም ከእርሱ ጋር ስለ ነበር የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር።


跟着我们:

广告


广告