Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 17:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራን እሰጠዋለሁ፥ በዚያም እተክለዋለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ ከእንግዲህም ወዲያ እንደ ቀድሞው ዘመን ዓመፀኞች አያስጨንቁትም፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የራሳቸውም መኖሪያ ስፍራ እንዲኖራቸው፣ ከእንግዲህ በኋላም እንዳይናወጡ ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ ስፍራ እሰጣቸዋለሁ። ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ክፉዎች ከእንግዲህ አይጨቍኗቸውም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9-10 ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ እዚያም በገዛ ምድራቸው በሰላም እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤ ግፈኞች እንደ ቀድሞው በፍጹም አያስጨንቁአቸውም፤ ከዚህ በፊት በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሳፍንትን እንደ ሾምኩበት ጊዜ ያለ ችግር ዳግመኛ አይደርስባቸውም፤ ጠላቶችህን ሁሉ አስገዛልሃለሁ፤ እኔ እግዚአብሔርም ንጉሣዊ ቤትህን እንደምሠራልህ እገልጥልሃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለሕ​ዝ​ቤም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስፍራ አደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለሁ፥ በዚ​ያም እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ፥ በስ​ፍ​ራ​ውም ይቀ​መ​ጣል፤ ከዚ​ያም በኋላ አይ​ና​ወ​ጥም፤ የኀ​ጢ​አ​ትም ልጆች እንደ ቀድ​ሞው አያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ትም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9-10 ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፤ እተክለውማለሁ፤ በስፍራውም ይቀመጣል፤ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ እንደ ቀድሞው ዘመንና በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ፈራጆች እንዳስነሣሁበት ጊዜ ግፈኞች ተመልሰው አያስጨንቁትም፤ ጠላቶችህንም ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ። እግዚአብሔር ደግሞ ቤት እንዲሠራልህ እነግርሃለሁ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 17:9
21 交叉引用  

ይህም የሆነው በእስራኤል ላይ ፈራጆች ባሥነሣሁ ጊዜ ነበር፤ ጠላቶችህንም ሁሉ በሥርህ እንዲገዙ አደርለሁ። ጌታ ደግሞ ቤት እንደሚሠራልህ እነግርሃለሁ።


በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆች ስም የአንተን ስም ታላቅ አደርጋለሁ።


አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።


እጄም ትረዳዋለች፥ ክንዴም ታጸናዋለች።


ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።


ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።


ልጆችሽ ይፈጥናሉ፥ ሊያፈረሱሽና ሊያወደሙሽ ከአንቺ ይወጣሉ።


ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጉስቁልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ።


ጌታ ለክብሩ የተከላቸው ጽድቃዊ የባሉጥ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች በአመድ ፋንታ አክሊልን እንዳደርግላቸው፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘን መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እንድሰጣቸው ልኮኛል።


ዓይኔንም ለበጐነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ወደዚህችም ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።


ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ደስ ይለኛል፥ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።


በጥበብህና በማስተዋልህ ሀብትን ለራስህ አግኝተሃል፥ ወርቅና ብርም በግምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብስበሃል።


ከሕዝቦች አወጣቸዋለሁ፥ ከአገሮች እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች ላይ፥ በፈሳሾች አጠገብ፥ በምድሪቱም መኖሪያ በሚሆኑ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።


ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት፥ አባቶቻችሁም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱ፥ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘለዓለም በእርሷ ይኖራሉ፤ አገልጋዬ ዳዊት ለዘለዓለም ልዑላቸው ይሆናል።


በምድራቸውም ላይ እተክላቸዋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም፥” ይላል ጌታ አምላክህ።


ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታላችሁ።


እንባዎችንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ላይ ይጠርጋል፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና።”


跟着我们:

广告


广告