1 ዜና መዋዕል 15:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 የጌታም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት ሲያሸበሽብና ሲዘል አይታ በልብዋ ናቀችው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም29 የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡ ዳዊት ሲደሰትና ሲያሸበሽብ ባየችው ጊዜ በልቧ ናቀችው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ታቦቱ ወደ ከተማይቱ በመግባት ላይ ሳለ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ንጉሥ ዳዊት በደስታ ሲያሸበሽብና ሲዘል በመስኮት ተመለከተች፤ በልብዋም ናቀችው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰች ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት ሲዘፍንና ሲጫወት አይታ በልብዋ ናቀችው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት ሲዘፍንና ሲጫወት አይታ በልብዋ ናቀችው። 参见章节 |