Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 15:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ዳዊትም፥ የእስራኤልም ሽማግሌዎች፥ የሻለቆችም የጌታን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዖቤድ-ኤዶም ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ስለዚህ ዳዊት የእስራኤል ሽማግሌዎችና የሻለቃው አዛዦች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት፥ የእስራኤል ሕዝብ መሪዎችና የጦር አዛዦች የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ ዖቤድኤዶም ቤት ሄዱ፤ ከፍ ያለ የደስታ ሥነ ሥርዓትም አደረጉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ዳዊ​ትም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ የሻ​ለ​ቆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት በደ​ስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ዳዊት፥ የእስራኤል ሽማግሌዎችና ሻለቆች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት በደስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 15:25
21 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት ለማምጣት፥ ወደ ቤተ መቅደሱም ለማስገባት፥ የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጐሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ።


ለጌታ ታቦት ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎለት ነበርና ዳዊት ከቂርያት-ይዓሪም ወዳዘጋጀለት ስፍራ ታቦቱን አምጥቶት ነበር።


በዚያን ጊዜም ሰሎሞን የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።


የእስራኤል ልጆች፥ ካህናትና ሌዋውያን የቀሩትም ምርኮኞች፥ የዚህን የእግዚአብሔርን ቤት ምረቃ በደስታ አከበሩ።


ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ከዚህ በኋላ የቀሩት ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።


ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጦሩ አዛዦች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ።


እኔም ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን አለቆች ተቀበልኩ፥ በእናንተም ላይ የሺህ አለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ የኀምሳ አለቆችም፥ የዐሥር አለቆችም ገዢዎችም በየነገዶቻቸው አደረግኋቸው።


አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮችህ፤ በከተሞችህ የሚኖር ሌዋዊም፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ፤ እጅህም በነካው ነገር ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይልሃል።


በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”


አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችህ፥ በከተሞችህ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ በመካከልህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች ጌታ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።


አምላክህ ጌታ በፍሬህ ሁሉ በእጅህም ሥራ ሁሉ ይባርክሃልና ጌታ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለጌታ ሰባት ቀን በዓል ታደርጋለህ፥ አንተም ፈጽሞ ደስ ይልሃል።


እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን በእውነትም ከተገረዙት ወገን የሆንን ነንና።


ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፤ ደስ ይበላችሁ።


ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ንቃችሁ፤ ‘የለም፤ ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ። ስለዚህ በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ሆናችሁ በጌታ ፊት ቅረቡ።”


ሳኦልም እንዲህ አላቸው፤ “እናንት የብንያም ሰዎች ስሙ! በውኑ የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋችኋልን?


አንዳንዶቹን ሻለቆችና አምሳ አለቆች ያደርጋቸዋል፤ ሌሎቹን መሬቱን እንዲያርሱና እህሉን እንዲያጭዱ፥ ሌሎቹን ደግሞ የጦር መሣሪያና ለሠረገላ የሚሆኑትን ዕቃዎች እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል።


跟着我们:

广告


广告