Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 15:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዳዊትም በራሱ ከተማ ላይ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔርም ታቦት ስፍራ አዘጋጀ፥ ድንኳንም ተከለለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዳዊት በስሙ በተጠራችው ከተማ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔር ታቦት ቦታ አዘጋጅቶ ድንኳን ተከለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዳዊት የሚኖርባቸውን ቤቶች በራሱ ከተማ በኢየሩሳሌም ሠራ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የሚኖርበትንም ስፍራ አዘጋጅቶ ድንኳን ተከለለት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዳዊ​ትም በከ​ተ​ማው ለራሱ ቤቶ​ችን ሠራ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ስፍራ አዘ​ጋጀ፤ ድን​ኳ​ንም ተከ​ለ​ላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዳዊትም በከተማው ላይ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔርም ታቦት ስፍራ አዘጋጀ፤ ድንኳንም ተከለለት።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 15:1
14 交叉引用  

ንጉሡ ግን፥ “እዚያው ቤቱ ይሂድ፤ ፊቴን ማየት የለበትም” አለ። ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ቤቱ ሄደ፤ ወደ ንጉሡም ፊት ቀርቦ አልታየም።


ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በምሽጉ ላይ አደረገ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራው። ዳዊትም ከሚሎ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ገነባው።


በዚህ ጊዜ፥ “በእግዚአብሔር ታቦት ምክንያት የዖቤድ ኤዶም ቤተሰቡና ያለውን ሁሉ ጌታ ባረከለት” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት ወደዚያው ወርዶ፥ የእግዚአብሔርን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በታላቅ ደስታ አመጣው።


ከዚያም የጌታን ታቦት አምጥተው፥ ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ በተዘጋጀለት ስፍራ አኖሩት፤ ዳዊትም የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት በጌታ ፊት አቀረበ።


እነርሱንም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናችሁ፤ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ የእስራኤልን አምላክ የጌታን ታቦት እንድታመጡ እናንተና ወንድሞቻችሁ ተቀደሱ።


ዳዊትም ወዳዘጋጀለት ስፍራ የጌታን ታቦት ለማምጣት እስራኤልን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።


የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕትም በጌታ ፊት አቀረቡ።


ዳዊትም ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በጌታ ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው።


ለጌታ ታቦት ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎለት ነበርና ዳዊት ከቂርያት-ይዓሪም ወዳዘጋጀለት ስፍራ ታቦቱን አምጥቶት ነበር።


በዚያን ጊዜም ሰሎሞን የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።


ለጌታ ስፍራ፥ ለያዕቆብ ኀያል ማደሪያ እስካገኝ ድረስ ብሎ።


እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያን ያገኝ ዘንድ ለመነ።


跟着我们:

广告


广告