Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 14:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ፍልስጥኤማውያንም ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደተቀባ ሰሙ፥ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ዳዊትን ሊፈልጉ ወጡ፤ ዳዊትም በሰማ ጊዜ እነርሱን ሊወጋቸው ወጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱን ፍለጋ በሙሉ ኀይላቸው ወጡ፤ ዳዊትም ይህን ሰምቶ ስለ ነበር ሊገጥማቸው ወጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ እርሱን ለመማረክ ሠራዊታቸውን አዘመቱ፤ ዳዊትም ይህን ሰምቶ ከእነርሱ ጋር ጦርነት ለመግጠም ወጣ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዳዊት በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ዳዊ​ትን ሊፈ​ልጉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም በሰማ ጊዜ ሊጋ​ጠ​ማ​ቸው ወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ፍልስጥኤማያንም ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደተቀባ ሰሙ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ዳዊትን ሊፈልጉ ወጡ፤ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ሊጋጠማቸው ወጣ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 14:8
8 交叉引用  

ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በጌታ ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም በእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን ቀቡት።


የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በጌታ ፊት ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደረገ፤ በሳሙኤልም አንደበት እንደ ተናገረው እንደ ጌታ ቃል በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን ቀቡት።


ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት ተብለው ይጠሩ ነበር።


ፍልስጥኤማውያንም መጥተው በራፋይም ሸለቆ አደጋ ጣሉ።


የአኪሽ አገልጋዮችም፥ “የምድሪቱ ንጉሥ ዳዊት ይህ አይደለምን? ደግሞስ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ፤ ዳዊት ዐሥር ሺህ ገደለ’ ብለው በጭፈራቸው የዘፈኑለትስ እርሱ አይደለምን?” አሉት።


跟着我们:

广告


广告