1 ዜና መዋዕል 11:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 እነዚህም ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት በመካከላቸው ጥሰው አለፉ፥ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን ሊጠጣ አልፈለገም፥ ነገር ግን ለጌታ እንደ መባ አፈሰሰው፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 በዚህ ጊዜ ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት መካከል ሰንጥቀው በማለፍ በቤተ ልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጕድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 በዚህን ጊዜ ሦስቱ ዝነኛ ወታደሮች የፍልስጥኤማውያንን ሰፈር ጥሰው በማለፍ ከጒድጓዱ ውሃ ቀዱና ለዳዊት ይዘውለት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጠጣው አልወደደም፤ በዚህ ፈንታ ለእግዚአብሔር እንደ መባ አድርጎ አፈሰሰው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 እነዚህ ሦስቱ ኀያላን የፍልስጥኤማውያንን ሰፈር ሰንጥቀው ሄዱ፥ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፤ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን ሊጠጣ አልወደደም፥ ነገር ግን ለእግዚአብሔር አፍስሶ፦ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እነዚህም ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ቀድደው ሄዱ፤ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውሃ ቀዱ፤ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን ሊጠጣ አልወደደም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር አፍስሶ 参见章节 |