Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘካርያስ 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፥ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፥ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እውነተኛ ፍትሕ አስፍኑ፣ እርስ በርሳችሁ ምሕረትና ርኅራኄን አድርጉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፤ እርስ በርሳችሁ ደግነትና ርኅራኄ ይኑራችሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “እኔ የሠራዊት አምላክ ለሕዝቤ የሰጠሁት ትእዛዝ ይህ ነበር፤ ‘በትክክል ፍረዱ፥ እርስ በርሳችሁም አንዳችሁ ለሌላው ምሕረትና ርኅራኄን አድርጉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፣ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፣ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥

参见章节 复制




ዘካርያስ 7:9
30 交叉引用  

ዳዊትም፦ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፥ የአባትህንም የሳኦልን ምድር ሁሉ እመልስልሃለሁ፥ አንተም ሁልጊዜ ከገበታዬ እንጀራ ትበላለህ አለው።


ጐንና ጐኑ ያልባረከችኝ፥ በበጎቼም ጠጕር ያልሞቀ እንደ ሆነ፥


ሁሉን የሚችለውን የአምላክን መፍራት ለሚተው፥ ለመዛል ለቀረበው ስንኳ ወዳጁ ቸርነትን ሊያሳይ ይገባል።


የዳዊት ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፥ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም አትበድሉ፥ አታምፁባቸውም፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።


ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፥ መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።


መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥


በአራጣ ባያበድር፥ ትርፎቻም ባይወስድ፥ እጁንም ከኃጢአት ቢመልስ፥ በሰውና በሰው መካከልም የእውነትን ፍርድ ቢፈርድ፥ በትእዛዜም ቢሄድ፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል አለቆች ሆይ፥ ይብቃችሁ፥ ግፍንና ብዝበዛን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ፥ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አርቁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፥ ምሕረትንና ፍርድን ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።


በፍርድ ዓመፃ አታድርጉ፤ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በእውነት ፍረድ።


ነገር ግን ፍርድ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም እንደማይደርቅ ፈሳሽ ይፍሰስ።


ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?


ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ በምቾትም ተቀምጠው ሳሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ የተናገረውን ቃል መስማት አይገባችሁምን?


የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።


ነገር ግን እናንተ ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከጤና አዳም ከአትክልትም ሁሉ አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና እግዚአብሔርን መውደድ ስለምትተላለፉ፥ ወዮላችሁ፤ ነገር ግን ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉት ይገባችሁ ነበር።


ቅን ፍርድ ፍረዱ እንጂ በመልክ አትፍረዱ።”


“ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ማንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” አላቸው።


የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፤ ወደ ወንድምህ መልሰው።


跟着我们:

广告


广告