Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘካርያስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እናንተ ሆይ፥ ከሰሜን ምድር ሽሹ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ኑ! ኑ! ውጡ፤ ከሰሜን ምድር አምልጡ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለአራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እኔም፦ “አንተ ወዴት ነው የምትሄደው?” አልኩት። እርሱም፦ “ኢየሩሳሌምን ልለካትና ወርድና ርዝመቷ ስንት መሆኑን ለማየት ነው የምሄደው” አለኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በየአራቱም ማእዘን በትኜአችሁ ነበር፤ አሁን ግን ከሰሜን ምድር ተነሥታችሁ ሽሹ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እናንተ ሆይ፥ ከሰሜን ምድር ሽሹ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እንደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ዘካርያስ 2:6
30 交叉引用  

ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኍላ እንዲህ አለው ራስህን አድን ወደ ኍላህ አትይ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ።


ከባቢሎን ውጡ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፥ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ ይህንም ንገሩ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፦ እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ታድጎታል በሉ።


እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፥ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ከሰሜን ወገን ክፉ ነገር በምድሪቱ በተቀመጡ ሁሉ ላይ ይገለጣል።


የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ በምድር መንግሥታት ሁሉ መካከል ለመከራ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


በዚያም ዘመን የይሁዳ ቤት ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳል፥ በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።


አሕዛብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፦ እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ።


ከሐናንኤል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ ከተማ ለእግዚአብሔር የሚሠራበት ዘመን፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።


እነሆ፥ ከሰሜን አገር አመጣቸዋለሁ፥ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፥ በመካከላቸውም ዕውሩና አንካሳው ያረገዘችና የወለደችም በአንድነት፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።


ከባቢሎን መካከል ሽሹ፥ ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፥ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ።


ሕዝቤ ሆይ፥ ከመካከልዋ ውጡ እያንዳንዳችሁም ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ራሳችሁን አድኑ።


ከሰይፍ ያመለጣችሁ ሆይ፥ ሂዱ፥ አትቁሙ፥ እግዚአብሔርን ከሩቅ አስቡ፥ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።


ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፥ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፥ በበደልዋ አትጥፉ፥ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታልና።


ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ፥ ወደ አገሮችም በትኛቸዋለሁ፥ ይሁን እንጂ፥ በመጡባቸው አገሮች በእነዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ በል።


ጭፍሮቹም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ የቀሩትም ሁሉ ወደ እየነፋሳቱ ይበተናሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ ታውቃላችሁ።


ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፥ ፍርድንም አደርግብሻለሁ ከአንቺም የቀረውን ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ።


ከአንቺም ሢሶው በቸነፈር ይሞታል፥ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፥ ሢሶውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል፥ ሢሶውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ በኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ።


እርሱም በተነሣ ጊዜ መንግሥቱ ይሰበራል፥ እስከ አራቱ የሰማይ ነፋሳት ይከፋፈላል። ለዘሩ ግን አይከፋፈልም፥ እንደ ገዛበትም አገዛዝ አይሆንም፥ መንግሥቱ ይነቀላልና፥ ከእነዚህም ለሌሎች ይሆናልና።


እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ እህልም በወንፊት እንዲነፋ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እነፋለሁ፥ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፥ ቤቴ ይሠራባታል፥ በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


አንቺ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ጽዮን ሆይ፥ ኰብልዪ።


መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።


በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል።


እግዚአብሔርም ከምድር ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ወዳሉ አሕዛብ ሁሉ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተና አባቶችህ ያላወቃችኋቸውን ሌሎችን አማልክት፥ እንጨትንና ድንጋይን፥ ታመልካለህ።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤


ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ “አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ፤” አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።


跟着我们:

广告


广告