Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሩት 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ሽማግሌዎቹም “እኛ ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፤ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፤ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚያም ሽማግሌዎቹና በከተማዪቱ በር አደባባይ የነበሩት ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “እኛ ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት፣ የእስራኤልን ቤት በአንድነት እንደ ሠሩ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፤ አንተም በኤፍራታ የበረታህ ሁን፤ ስምህም በቤተ ልሔም የተጠራ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ፦ “እኛ ምስክሮች ነን፥ ጌታ ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ፥ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፥ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተልሔም ይጠራ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች እንዲህ አሉ፥ “አዎ፥ እኛ ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ሚስትህን ብዙ ልጆችን በመውለድ የያዕቆብን ቤት እንደ መሠረቱት እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርግልህ፤ እግዚአብሔር በኤፍራታ ያበልጽግህ፤ በቤተልሔምም ዝነኛ ያድርግህ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ሽማግሌዎቹም፦ እኛ ምስክሮች ነን፣ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፣ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።

参见章节 复制




ሩት 4:11
24 交叉引用  

ኤፍሮን፥ በኬጢ ሰው ኤፍሮን፥ የኬጢ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሁሉ ሲሰሙ


ርብቃንም መረቁአትና፦ አንቺ እኅታችን እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላቶችን ደጅ ይውረስ አሉአት።


ለላባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱ ስም ራሔል ነበረ።


በነጋም ጊዜ እንሆ ልያ ሆና ተገኘች፤ ላባንም፦ ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለግልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ? አለው።


ልያም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙም ሮቤል ብላ ጠራችው እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና።


የያዕቆብም ልጆች አሥራ ሁለት ናቸው የልያ ልጆች የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤


የራሔል ልጆች ዮሴፍ፥ ብንይም፤


ሽማግሌዎችም ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ፦ አትስማው፥ እሺም አትበለው አሉት።


የቤተ ልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት ጋዴር አባት ሐሬፍ።


በውሉም ወረቀት ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፥ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት።


አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳይቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ፦ ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔ ጋር ሊኖርም አልወደደም ትበላቸው።


ዋርሳይቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል ስትል ጭማውን ከእግሩ ታውጣ፥ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።


የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፤ የቤተ ልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።


跟着我们:

广告


广告