Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሩት 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ቦዔዝም ከበላና ከጠጣ ሰውነቱንም ደስ ካሰኘ በላ፥ በእህሉ ክምር አጠገብ ሊተኛ ሄደ፤ ሩትም በቀስታ መጣች፤ እግሩንም ገልጣ ተኛች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ቦዔዝ በልቶ ጠጥቶ ከጨረሰና ደስም ከተሠኘ በኋላ፣ ራቅ ካለው የእህል ክምር አጠገብ ለመተኛት ሄደ። ሩት በቀስታ ከአጠገቡ ደረሰች፤ እግሩንም ገልጣ ተኛች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ቦዔዝም ከበላና ከጠጣ ሰውነቱንም ደስ ካሰኘ በኋላ፥ በእህሉ ክምር አጠገብ ሊተኛ ሄደ፥ ሩትም በቀስታ መጣች፥ እግሩንም ገልጣ ተኛች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ቦዔዝ ከበላና ከጠጣ በኋላ ደስ ብሎት ነበር፤ ወደ ገብሱም ክምር ሄዶ ጋደም አለና አንቀላፋ፤ ሩትም በቀስታ ወደ እርሱ ተጠጋች፤ ልብሱንም ገለጥ አድርጋ በእግሩ አጠገብ ተኛች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ቦዔዝም ከበላና ከጠጣ ሰውነቱንም ደስ ካሰኘ በኋላ፥ በእህሉ ክምር አጠገብ ሊተኛ ሄደ፣ ሩትም በቀስታ መጣች፥ እግሩንም ገልጣ ተኛች።

参见章节 复制




ሩት 3:7
18 交叉引用  

በፊቱም ካለው መብል ፈንታቸውን አቀረበላቸው የብንያም ፈንታ ከሁሉ አምስት እጅ የሚበልጥ ነበረ እነርሱም ጠጡ ከእርሱም ጋር ደስ አላቸው።


አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፥ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም፥ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው።


የእስራኤልም ንጉሥ የአገሩን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ፦ ተመልከቱ፥ ይህም ሰው ክፉ እንዲሻ እዩ፤ ስለ ሴቶቼ ስለ ልጆቼ ስለ ብሬና ወርቄም ላከብኝ፥ እንቢም አላልሁም አለ።


በሰባተኛውም ቀን ንጉሡ አርጤክስስ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ደስ ባለው ጊዜ፥ ንግሥቲቱ አስጢን መልከ መልካም ነበረችና ውበትዋ ለአሕዛብና ለአለቆች እንዲታይ የመንግሥቱን ዘውድ ጭነው ወደ ንጉሡ ፊት ያመጡአት ዘንድ በፊቱ የሚያገለግሉትን ሰባቱን ጃንደረቦች ምሁማንን፥ ባዛንን፥ ሐርቦናን፥ ገበታን፥ ዘቶልታን፥ ዜታርን፥ ከርከስን አዘዛቸው።


እንጀራን ለሳቅ የወይን ጠጅንም ለሕይወት ደስታ ያደርጉታል፥ ሁሉም ለገንዘብ ይገዛል።


ለሰው ከሚበላና ከሚጠጣ በድካሙም ደስ ከሚለው በቀር የሚሻለው ነገር የለም፥ ይህም ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።


ከሚበላውና ከሚጠጣው ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሐይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፥ ከፀሐይም በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ይህ ደስታው ከእርሱ ጋር ይኖራል።


እግዚአብሔር ሥራህን ተቀብሎታልና ሂድ፥ እንጀራህን በደስታ ብላ፥ የወይን ጠጅህንም በተድላ ጠጣ።


እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።


መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤


ልባቸውንም ደስ ባለው ጊዜ፦ በፊታችን እንዲጫወት ሶምሶንን ጥሩት አሉ። ሶምሶንንም ከግዞት ቤት ጠሩት፥ በፊታቸውም ተጫወተ፥ ተዘባበቱበትም፥ በምሰሶና በምሰሶም መካከል አቆሙት።


ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ ወስላቶች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ በሩንም ይደበድቡ ነበር፥ ባለቤቱንም ሽማግሌውን፦ ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን አሉት።


ተቀመጡም በአንድ ላይም በሉ ጠጡም፥ የብላቴናይቱም አባት ሰውዮውን፦ ዛሬ ደግሞ ከዚህ ለማደር፥ እባክህ፥ ፍቀድ፥ ልብህንም ደስ ይበለው አለው።


ሰውዮውም ከቁባቱና ከአሽከሩ ጋር ለመሄድ በተነሣ ጊዜ የብላቴናይቱ አባት አማቱ፦ እነሆ፥ ቀኑ ተዋግዶአል፥ በዚህ እደሩ፥ እነሆ፥ ቀኑ ለማለፍ ተዋግዶአል፥ ልባችሁ ደስ እንዲለው በዚህ እደሩ፥ ነገም ወደ ቤታችሁ እንድትደርሱ ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለው።


ወደ አውድማውም ወረደች፤ አማትዋም ያዘዘቻትን ሁሉ አደረገች።


መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፤ ዘወርም አለ፤ እነሆም፥ አንዲት ሴት በእግርጌው ተኝታ ነበረች።


跟着我们:

广告


广告