Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሩት 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እርስዋም ‘ከአጫጆቹ በኋላ በነዶው መካከል እንድቃርምና እንድለቅም እባክህ ፍቀድልኝ’ አለች፤ መጣችም፤ ከማለዳም ጀምራ እስከ አሁን ድረስ ቆይታለች፤ በቤትም ጥቂት ጊዜ እንኳ አላረፈችም፤” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እርሷም፣ ‘ዐጫጆቹን እየተከተልሁ በነዶው መካከል እንድቃርም እባክህ ፍቀድልኝ’ አለችኝ። ለጥቂት ጊዜ በመጠለያው ከማረፏ በቀር፣ ወደ አዝመራው ቦታ ገብታ ከጧት አንሥቶ እስካሁን ያለ ማቋረጥ ስትቃርም ቈይታለች።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “እርሷም፦ ‘ከአጫጆቹ በኋላ በነዶው መካከል እንድቃርምና እንድለቅም፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ’ ብላ፥ መጣች፤ ከማለዳም ጀምራ እስከ አሁን ስትቃርም ቆይታለች፤ በቤትም ጥቂት ጊዜ እንኳ አላረፈችም” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አጫጆችን ተከትላ ከነዶ መካከል የወዳደቀውን ዛላ ለመቃረም እንድፈቅድላት ጠየቀችኝ፤ ከጧት ጀምራ እስከ አሁን ስትቃርም ነበር፤ አሁን ግን ትንሽ ዕረፍት ለማድረግ ወደ ዳስ ተጠግታለች።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እርስዋም፦ ከአጫጆቹ በኋላ በነዶው መካከል እንድቃርምና እንድለቅም፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ አለች፣ መጣችም፥ ከማለዳም ጀምራ እስከ አሁን ድረስ ቆይታለች፣ በቤትም ጥቂት ጊዜ እንኳ አላረፈችም አለው።

参见章节 复制




ሩት 2:7
14 交叉引用  

አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።


ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤


ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት።


ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።


ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን “በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ፤” አለቻት። እርስዋም “ልጄ ሆይ! ሂጂ፤” አለቻት።


ሞዓባዊቱ ሩትም “ደግሞ ‘መከሬን እስኪጨርሱ ድረስ ጐበዛዝቴን ተጠጊ፤’ አለኝ፤” አለቻት።


የአጫጆቹም አዛዥ “ይህችማ ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ሞዓባዊቱ ቆንጆ ናት፤


ቦዔዝም ሩትን “ልጄ ሆይ! ትሰሚያለሽን? ቃርሚያ ለመቃረም ወደ ሌላ እርሻ አትሂጂ፤ ከዚህም አትላወሺ፤ ነገር ግን ገረዶቼን ተጠጊ።


跟着我们:

广告


广告