ዘኍል 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እነዚያም ሰዎች፦ በሞተ ሰው ሬሳ ረክሰናል፤ በእስራኤል ልጆች መካከል በጊዜው ቍርባን ለእግዚአብሔር እንዳናቀርብ ስለ ምን እንከለከላለን? አሉት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ሙሴን፣ “በሬሳ ምክንያት ረክሰናል፤ ታዲያ የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነን በተወሰነው ጊዜ እንዳናቀርብ ለምን እንከለከላለን?” አሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እነዚያም ሰዎች እርሱን እንዲህ አሉት፦ “የሞተውን ሰው ሬሳ በመነንካት ብንረክስም እንኳ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል የጌታን ቁርባን በተወሰነለት ጊዜ እንዳናቀርብ ለምን እንከለከላለን?” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 “እኛ በድን በመንካታችን ረክሰናል፤ ነገር ግን ከቀሩት እስራኤላውያን ተለይተን በወቅቱ ለእግዚአብሔር መባ እንዳናቀርብ ስለምን እንከለከላለን?” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 በዚያም ቀን ወደ ሙሴና ወደ አሮን ቀረቡ። እነዚያም ሰዎች “እኛ በሰውነታችን ርኵሰት ያለብን ሰዎች ነን፤ በእስራኤል ልጆች መካከል በጊዜው ቍርባን ለእግዚአብሔር እንዳናቀርብ ስለ ምን እንከለከላለን?” አሉት። 参见章节 |