Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 8:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሌዋውያንም ከኃጢአት ተጣጠቡ፥ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ስጦታ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፥ አሮንም ያነጻቸው ዘንድ አስተሰረየላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሌዋውያኑ ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሶቻቸውንም ዐጠቡ፤ ከዚያም አሮን እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፤ እንዲነጹም ማስተስረያ አደረገላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሌዋውያንም ከኃጢአት ራሳቸውን አነጹ፥ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት አቀረባቸው፥ አሮንም እነርሱን ለማንጻት ማስተስረያ አደረገላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሌዋውያንም ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ አድርጎ ለእግዚአብሔር ለያቸው የመንጻቱንም ሥርዓት ፈጸመላቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሌዋ​ው​ያ​ንም ከኀ​ጢ​አት ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አጠቡ፤ አሮ​ንም ስጦታ አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ አሮ​ንም ያነ​ጻ​ቸው ዘንድ አስ​ተ​ሰ​ረ​የ​ላ​ቸው።

参见章节 复制




ዘኍል 8:21
10 交叉引用  

እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገም ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤


የሚያነጻውም ካህን እነዚህን ነገሮች የሚነጻውንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ያኖራቸዋል።


በዚህም ውኃ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ያጠራል፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያጠራ ንጹሕ አይሆንም።


ንጹሑም በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን በርኩሱ ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ያጠራዋል፤ እርሱም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ በማታም ጊዜ ንጹሕ ይሆናል።


እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ማኅፀን በሚከፍተው በበኵሩ ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤


ከዚያም በኋላ ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ፤ ታነጻቸውማለህ፥ ስጦታም አድርገህ ታቀርባቸዋለህ።


ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው።


ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ይሠሩ ዘንድ ገቡ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው።


ታነጻቸው ዘንድ እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ሁሉ ምላጭ ያሳልፉ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ይታጠቡም።


跟着我们:

广告


广告