Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 7:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 መሠዊያውም በተቀባ ቀን አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ ቍርባንን አቀረቡ፤ አለቆችም መባቸውን በመሠዊያው ፊት አቀረቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 መሠዊያው በተቀባበት ቀን አለቆች የመሠዊያውን መቀደስ ምክንያት በማድረግ ስጦታዎችን አመጡ፤ በመሠዊያውም ፊት አቀረቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 መሠዊያውም በተቀባ ቀን አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ ቁርባንን አቀረቡ፤ አለቆችም መባቸውን በመሠዊያው ፊት አቀረቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 መሠዊያው በተባረከበት ቀን መሪዎቹ መሠዊያውን ለመቀደስ በመሠዊያው ፊት ቊርባን አቀረቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 መሠ​ዊ​ያ​ውም በተ​ቀባ ቀን አለ​ቆቹ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ ቍር​ባ​ንን አቀ​ረቡ፤ አለ​ቆ​ችም መባ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት አቀ​ረቡ።

参见章节 复制




ዘኍል 7:10
12 交叉引用  

ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ይሠዋ ዘንድ ለደኅንነት መሥዋዕት ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሃያ ሺህ በጎች አቀረበ። ንጉሡና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲሁ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ።


ንጉሡም ሰሎሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሃያ ሺህ በጎች ሠዋ። እንዲሁ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ።


ሰባት ቀንም መሠዊያውን ቀድሰው፥ ሰባት ቀንም በዓል አድርገው ነበርና በስምንተኛው ቀን የተቀደሰውን ጉባኤ አደረጉ።


የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርም በጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።


እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፥ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፥ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ።


እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ማደሪያውን ፈጽሞ ከተከለ በኋላ፥ እርሱንና ዕቃውን ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፤


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ መባቸውን እያንዳንዱ በቀን በቀኑ ያቅርቡ አለው።


መሠዊያው በተቀባ ቀን የእስራኤል አለቆች ለመቀደሻው ያቀረቡት ቍርባን ይህ ነበረ፤ አሥራ ሁለት የብር ወጭቶች፥ አሥራ ሁለት የብር ድስቶች፥ አሥራ ሁለት የወርቅ ጭልፋዎች፤


የደኅንነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ ሀያ አራት በሬዎች፥ ስድሳም አውራ በጎች፥ ስድሳም አውራ ፍየሎች፥ ስድሳም የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቀደሻው የቀረበ ቍርባን ይህ ነበረ።


አለቆችም ለሕዝቡ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ሰው ቢኖር በሰልፍ እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያስመረቀው ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።


跟着我们:

广告


广告