Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 6:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ራሱን የተለየ ባደረገበት ወራት ሁሉ ከወይን የሆነውን ነገር ሁሉ ከውስጡ ፍሬ ጀምሮ እስከ ገፈፎው ድረስ አይብላ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በናዝራዊነቱ ወቅት ከወይን ተክል የሚገኘውን ማንኛውም ነገር፣ የወይኑን ዘር፣ ግልፋፊውንም እንኳ ቢሆን አይብላ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ከወይን ጠጅ የሚሠራውን ሌላ ነገር ሁሉ እንዲሁም የውስጡን ፍሬ ወይም ግልፋፊውን እንኳ አይብላ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በናዝራዊነቱ ወቅት ከወይን ሐረግ የሚገኘውን ሁሉ የወይኑን ፍሬ ግልፋፊ ወይም ዘር አይብላ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ራሱን የተ​ለየ ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ከወ​ይን የሆ​ነ​ውን ነገር ሁሉ ከው​ስጡ ፍሬ ጀምሮ እስከ ደረ​ቀው ዘቢብ ድረስ አይ​ብላ።

参见章节 复制




ዘኍል 6:4
7 交叉引用  

ስእለቱን የተሳለው የናዝራዊ፥ እጁም ከሚያገኘው ሌላ ስለ ናዝራዊነቱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የቍርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ናዝራዊነቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል።


ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን የተለየ ያድርግ፤ ከወይን ወይም ከሌላ ነገር የሚገኘውን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ የወይንም ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን እሸት ወይም ዘቢብ አይብላ።


ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይደርስም፤ ለእግዚአብሔር የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም ጠጕር ያሳድጋል።


ከወይንም ከሚወጣው ሁሉ አትብላ፥ የወይን ጠጅንም የሚያሰክርንም ነገር አትጠጣ፥ ርኩስም ነገር ሁሉ አትብላ፥ ያዘዝኋትን ሁሉ ትጠብቅ አለው።


跟着我们:

广告


广告