ዘኍል 5:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፥ ካህኑም ሴቲቱን፦ እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለሰለ ሆድሽንም እየነፋ፥ እግዚአብሔር ለመርገምና ለመሐላ በሕዝብሽ መካከል ያድርግሽ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እዚህ ላይ ካህኑ እንዲህ በማለት ሴትዮዋን በርግማን መሐላ ያስምላታል፤ “እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለለና ሆድሽን እያሳበጠ በሕዝብሽ መካከል ርግማንና መሐላ ያድርግብሽ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፥ ካህኑም ሴቲቱን እንዲህ ይላታል፦ ‘ጌታ ጭንሽን እያመነመነ ሆድሽንም እየነፋ፥ በሕዝብሽ መካከል ጌታ ለመርገምና ለመሐላ የምትሆኚ ያድርግሽ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ካህኑ ሴቲቱን እንዲህ ብሎ የመርገም መሐላ ያስሞላት፦ ‘እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለሰለና ሆድሽን እየነፋ በሕዝብሽ መካከል ለመሓላና ለእርግማን የተገባሽ ያድርግሽ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፤ ካህኑም ሴቲቱን እንዲህ ይበላት፦ እግዚአብሔር የተረገምሽ ያድርግሽ ጎንሽን ያረግፈው ዘንድ እግዚአብሔር ከሕዝብሽ መካከል ለይቶ ያጥፋሽ፤ ሆድሽን ይሰንጥቀው፤ 参见章节 |