ዘኍል 4:41 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ፥ ከጌድሶን ልጆች ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም41 ይህ ከጌርሶን ጐሣዎች በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉት ሰዎች ጠቅላላ ድምር ነው፤ እግዚአብሔር በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሙሴና አሮን እነዚህን ቈጠሯቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ፥ ከጌድሶን ልጆች ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉትና ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው የጌርሾን ልጆች እነዚህ ናቸው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ የጌድሶን ልጆች ቍጥር ይህ ነው። 参见章节 |