Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 4:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን መጋረጃ፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፥ አውታሮቻቸውንም፥ ለማገልገልም የሚሠሩበትን ዕቃ ሁሉ ይሸከሙ፤ በዚህ ያገልግሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እንዲሁም በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን የአደባባዩን መጋረጃዎች፣ የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፣ ገመዶችና ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ሁሉ ይሸከሙ፤ በዚህም ያገልግሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የአደባባዩንም መጋረጆች፥ በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለውን የአደባባዩን ደጃፍ መግብያ መጋረጃ፥ አውታሮቻቸውንም፥ የሚገለገሉባቸውንም ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ እነርሱንም በሚመለከት ሊደረግ የሚገባውን ነገር ሁሉ ያድርጋሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እንዲሁም በድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ለሚገኘው አደባባይ የተሠሩትን መጋረጃዎችና አውታሮች፥ ለአደባባዩ መግቢያ በር የሚሆኑትን መጋረጃዎችና ለእነዚህ መገልገያ የተመደቡትን ሌሎችንም ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ ለእነዚህም ዕቃዎች የሚሆነውን ማንኛውንም አገልግሎት ይፈጽማሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ያለ​ውን የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥ ለማ​ገ​ል​ገ​ልም የሚ​ሠ​ሩ​በ​ትን ዕቃ ሁሉ ይሸ​ከሙ፤ በዚ​ህም ያገ​ል​ግሉ።

参见章节 复制




ዘኍል 4:26
4 交叉引用  

የማደሪያውንም አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ ወገን የጥሩ በፍታ መጋረጆች ይሁኑለት፥ የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤


የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩንም ካስማዎች አውታሮቻቸውንም፤


አደባባዩንም አደረገ፤ በደቡብ ወገን ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ፥ የተፈተለ የጥሩ በፍታ መጋረጆች ነበሩ።


የጌድሶናውያን አገልግሎት ሁሉ፥ ሸክማቸውም ሁሉ፥ ሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ የሚደርስባቸውንም ሸክም ሁሉ ትነግሩአቸዋላችሁ።


跟着我们:

广告


广告