Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሚያገለግሉበትን ዕቃውን ሁሉ፥ ማንደጃዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ድስቶቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚያም ለመሠዊያው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች በሙሉ፣ የእሳት ማንደጃዎቹን፣ ሜንጦዎቹን፣ የእሳት መጫሪያዎቹንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን በላዩ ላይ ያድርጉ፤ በእነዚህም ላይ የአቆስጣ ቍርበት መሸፈኛ አልብሰው መሎጊያዎቹን በየቦታቸው ያስገቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በእርሱም ላይ የሚገለገሉባቸውን የመሠውያውን ዕቃዎች ሁሉ፥ ጀሞዎቹን ሜንጦቹንም መጫሪያዎቹንም ጐድጓዳ ሳሕኖቹንም፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም ላይ የአቆስጣን ቁርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በመሠዊያው ላይ ለማገልገል የሚጠቅሙትን ዕቃዎች፥ ማለትም ማንደጃዎችን፥ ሜንጦዎችን፥ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ያስቀምጡበት፤ የተለፋውንም ስስ ቊርበት በላዩ ደርበው መሎጊያዎችን ያስገቡበት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ዕቃ​ውን ሁሉ፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹን፥ ሜን​ጦ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንም፥ መክ​ደ​ኛ​ዎ​ቹ​ንም፥ ያመድ ማፍ​ሰ​ሻ​ዎ​ቹን፥ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ዕቃ ሁሉ ያስ​ቀ​ም​ጡ​በት፤ በእ​ር​ሱም የአ​ቆ​ስ​ጣን ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይዘ​ርጉ፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ። ሐም​ራ​ዊ​ዉ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ወስ​ደው ማስ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ው​ንና ማስ​ቀ​መ​ጫ​ውን ይሸ​ፍ​ኑት፤ በአ​ቆ​ስ​ጣው ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስ​ጥም አድ​ር​ገው በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ዎቹ ላይ ያኑ​ሩት፤

参见章节 复制




ዘኍል 4:14
7 交叉引用  

ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን ዕቃ ሁሉ፥ የወርቁንም መሠዊያ፥ የገጹንም ኅብስት የነበረባቸውን ገበታዎች፥


ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ መሠዊያ ከግራር እንጨት አድርግ፤ አራት ማዕዘንም ይሁን፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ይሁን።


አመድ የሚሆንባቸውን ምንቸቶች፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦቹንም፥ ማንደጃዎቹንም አድርግ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አድርግ።


አመዱንም ከመሠዊያው ላይ ያስወግዱ፥ ሐምራዊውንም መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤


ከሰፈሩም ሲነሡ፥ አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በመገናኛው ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


በላዩም የአስቆጣውን ቁርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፥ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።


跟着我们:

广告


广告