Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 35:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እስኪሞት ድረስ በጥላቻ ቢደፋው፥ ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢጥልበት፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አንድ ሰው ዐስቦበት ሌላውን በክፋት ገፍትሮ ቢጥለው ወይም እንዲሞት ሆነ ብሎ አንዳች ነገር ቢወረውርበት

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እስኪሞት ድረስ በጥላቻ ገፍትሮ ቢጥለው፥ ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢጥልበት፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “አንድ ሰው ሌላውን ሰው በጥላቻ ቢገፋው ወይም ሸምቆ አንዳች ነገር ቢወረውርበትና ይህ አድራጎቱ ሞትን ቢያስከትል፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጥል ቢጣ​ላው፥ ወይም ሸምቆ አን​ዳች ነገር ቢጥ​ል​በት፥ ቢሞ​ትም፥

参见章节 复制




ዘኍል 35:20
30 交叉引用  

ቃየንም እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ።


ቃየንም ወንድሙን አቤልን፤ ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፤ ገደለውም።


አቤሴሎምም እኅቱን ትዕማርን ስላሳፈራት አምኖንን ጠልቶታልና አቤሴሎም አምኖንን ክፉም ሆነ መልካምም አልተናገረውም።


አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፥ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፥ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፥ ሁለተኛም አልወጋውም፥ ሞተም።


አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም።


ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውን በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲሞት ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው።


ደም ተበቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳዩን ይግደል፤ ባገኛው ጊዜ ይግደለው።


ወይም በጥላቻ እስኪሞት ድረስ በእጁ ቢመታው፥ የመታው ፈጽሞ ይገደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም ተበቃዩ ባገኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው።


ሄሮድያዳ ግን ተቃውማው ልትገድለው ትፈልግ ነበር አልቻለችም፤


ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤


በዚያም ሦስት ወር ተቀምጦ ወደ ሶርያ በመርከብ ሊሄድ ባሰበ ጊዜ፥ አይሁድ ሴራ ስላደረጉበት በመቄዶንያ አልፎ ይመለስ ዘንድ ቆረጠ።


እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ አለው።


ሰው ግን ባልንጀራውን ቢጠላ፥ ቢሸምቅበትም፥ ተነሥቶም እስኪሞት ድረስ ቢመታው፥ ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥


ሳኦልም ዳዊትን በፍልስጥኤማውያን እጅ ይጥለው ዘንድ አስቦ፦ የንጉሥን ጠላቶች ይበቀል ዘንድ ከመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይሻም ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት አላቸው።


ዳዊትም ከአርማቴም አገር ከነዋትዘራማ ሸሸ፥ ወደ ዮናታንም መጥቶ፦ ምን አደረግሁ? እኔንስ ለመግደል የሚፈልግ በአባትህ ፊት ጠማምነቴና ኃጢአቴ ምንድር ነው? ብሎ ተናገረው።


ደግሞም፥ አባቴ ሆይ፥ የልብስህ ዘርፍ በእጄ እንዳለ ተመልክተህ እወቅ፥ የልብስህንም ዘርፍ በቆረጥሁ ጊዜ አልገደልሁህም፥ ስለዚህም በእጄ ክፋትና በደል እንደሌለ፥ አንተም ነፍሴን ልትወስድ ምንም ብታሳድደኝ እንዳልበደልሁህ ተመልክተህ እወቅ።


跟着我们:

广告


广告