ዘኍል 31:28 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ከእነዚያም ከተዋጉት ወደ ሰልፍም ከወጡት ሰልፈኞች ዘንድ፥ ከሰዎችም ከበሬዎችም ከአህዮችም ከመንጎችም ከአምስት መቶ አንድ ለእግዚአብሔር ግብር አውጣ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም28 በጦርነቱ ከተካፈሉት ወታደሮች ድርሻ ላይ፣ ከሰውም ሆነ ከቀንድ ከብት፣ ከአህያ፣ ከበግ ወይም ከፍየል ከየዐምስት መቶው አንዱን ለእግዚአብሔር ግብር አውጣ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ከእነዚያም ወደ ጦርነት ወጥተው ከተዋጉት ወታደሮች ድርሻ፥ ከሰዎችም ከበሬዎችም ከአህዮችም ከበጎችም ከአምስት መቶ አንድ ለጌታ ግብር አውጣ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ለወታደሮቹ ከተመደበው ክፍል፥ ከአምስት መቶ እስረኞች አንዱን፥ እንዲሁም ከከብቱ፥ ከአህዮቹ፥ ከበጎቹና ከፍየሎቹ ከአምስት መቶው አንዱን እጅ ለእኔ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ ለዩ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ከእነዚያም ከተዋጉት፥ ወደ ሰልፍም ከወጡት ሰልፈኞች ዘንድ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከአምስት መቶ አንድ ለእግዚአብሔር ግብር ታወጣላችሁ። 参见章节 |