Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 26:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ያም ወገን በሞተ ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ በዚያም ጊዜ እሳቲቱ ሁለት መቶ አምሳውን ሰዎች አቃጠለቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሁለት መቶ ዐምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከርሱ ጋራ ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ያም ወገን በሞተ ጊዜ፥ እሳቲቱም ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች ባቃጠለች ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ እነርሱን ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነርሱንም ምድር ተከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም በሞቱ ጊዜ እሳት ወርዶ ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች አቃጠላቸው፤ ለሕዝቡም መቀጣጫ ሆኑ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ማኅ​በ​ሩም በሞቱ ጊዜ ምድ​ሪቱ አፍ​ዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠ​ቻ​ቸው፤ በዚ​ያም ጊዜ እሳ​ቲቱ ሁለት መቶ አም​ሳ​ውን ሰዎች አቃ​ጠ​ለ​ቻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ለም​ል​ክት ሆኑ።

参见章节 复制




ዘኍል 26:10
15 交叉引用  

የእስራኤልም ልጆች ወደሚኖሩባት ምድር እስኪመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ።


ከእነርሱም የተነሣ በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ፦ የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ እግዚአብሔር ያድርግህ የምትባል እርግማንን ያነሣሉ፥ እኔም አውቃለሁ ምስክርም ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ፊቴንም በዚያ ሰው ላይ አደርጋለሁ ምልክትና ምሳሌም አደርገዋለሁ ከሕዝቤም መካከል አጠፋዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


ከእስራኤልም ልጆች ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች ከእነርሱ ጋር ወሰዱ፤ ከጉባኤው የተመረጡ ዝናቸውም የተሰማ የማኅበሩ አለቆች ነበሩ።


በኃጢአታቸው ሰውነታቸውን ያጠፉትን የእነዚያን ሰዎች ጥናዎች ጠፍጥፈህ ለመሠዊያ መለበጫ አድርጋቸው፤ በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋቸዋልና የተቀደሱ ናቸው፥ ለእስራኤልም ልጆች ምልክት ይሆናሉ።


አንድ በትርም ለአባቶቻቸው ቤት አለቃ ይሆናልና በሌዊ በትር ላይ የአሮንን ስም ጻፍ።


አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኃጢአት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእግዚአብሔር ላይ በተሰበሰቡ ወገን መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም።


በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተሰቦቻቸውን ድንኳኖቻቸውንም ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ በኤልያብ ልጆች በዳታንና በአቤሮን ያደረገውን ላላወቁትና ላላዩት ልጆቻችሁ አልነግራቸውምና እናንተ ዛሬ እወቁ።


በአንተም በልጅ ልጅህም ላይ ለዘላለም ለምልክትና ለድንቅ ይሆናሉ።


ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥


እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።


ይህ በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚመጣ ለአንተ ምልክት ነው፥ ሁለቱ በአንድ ቀን ይሞታሉ።


跟着我们:

广告


广告